መጥፎ የአፍጠረንን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ማድረግ ያለብዎትን ያውቃሉ? – Do You Know What to Do To Prevent or Reduce Bad Breath?

                                                             

1) የአፍዎን ንጽህና በሚገባ ይጠብቁ፡- ጥርስዎን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ማጽዳት እንዳለብዎ ይወቁ ከተቻለ ከምሳ በኋላም ለማጽዳት የጥርስ ብሩሽና የጥርስ ሳሙና በቦርሳዎ በመያዝ ጥርስዎን ያፅዱ፡፡

2) ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ፡- ውሃን መጠጣት በአፍ ውስጥ እርጥበትን ሰለሚፈጥር በብዛት እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ ከስኳር ነፃ ሆኑ ማስቲካዎችና ከረሜላዎች መውሰድ በአፍ ውስጥ (Saliva) ምራቅ እንዲመነጭ በማድረግ በአፍ ውስጥ የቀሩ ምግብና ባክቴሪያዎችን እንዲያጥብ ያደርጋል፡፡

3) ሲጋራን ማጤስ ማቆም፡- ሲራጋ ማጤስ ለመጥፎ የአፍ ጠረን መኖር ምክንያት ስለሚሆን
ማቆም ይኖርብዎታል፡፡

4) የሚወስዱትን ምግብ ወይንም መድኃኒት መጥፎ የአፍ ጠረን እንደሚያመጣብዎ ካወቁ ወደጥርስ ሐኪምዎ በመሄድ ማሳየት ተገቢ ነው፡፡

5) የጥርስ ሐኪምዎን በዓመት አንዴ እንዲያይዎት ማድረግ እንዲሁም በሕክምና የታገዘ ባለሙያዊ የጥርስ ዕጥበት በዓመት አንድ ጊዜ ማድረግ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement