ቻይና በ2020 በሰዓት 600 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ባቡር ገንብታ ለሙከራ እንደምታበቃ ገለፀች – China To Test 600 km/h Maglev Train by 2020

                                                                   

ቻይና በአውሮፓውያኑ 2020 በሰዓት እስከ 600 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ባቡር ገንብታ ለሙከራ ዝግጁ ለማድረግ ማቀዷን አስታወቀች።

የሀገሪቱ የባቡር ማምረቻ ኢንዳስትሪ እንዳስታወቀው ሊገነባ የታቀደው ባቡሩ የቴክኒክ ክፍል በእቅድ ደረጃ ከሲ አር አር ሲ ኩባንያ በተውጣጡ 19 ባለሙያዎች ፀድቋል።                                                                               

የኩባንያው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲንግ ሳንሳን እንዳስታቁት፥ እቅዱ የተገመገመ እንደመሆኑ ስራው ወደ ዲዛይን ግንባታ ይሸጋገራል።

በዚህም “በተያዘው እቅድ መሰረት በአውሮፓውያኑ 2018 አንድ ናሙና ይሰራል፤ የባቡሩ ሙሉ ተሽከርካሪ ደግሞ በ2020 በአምስት ኪሎ ሜትር ሀዲድ ላይ ይሞከራል” ብለዋል። 

የከፍተኛ ፍጥነት የባቡር ትራንስፖርት ስርዓት የማስተዋወቅ ሂደቱ፥ በሀገሪቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ 13ኛው የአምስት ዓመት ዕቅድ (2016-2020) ከተያዙት ቁልፍ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ አላማ ቻይና በከፍተኛ ፍጥነት የሚንቀሳቀሱ ትላልቅ የባቡር ቴክኖሎጂ ንድፍ፣ ማምረቻ፣ ማስተካከያ እና ግምገማ ስርዓቱን በመቆጣጠር የራሷ የሆነ አቅም እንዲኖራት ለማድረግ ነው ተብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement