ጆርጅ ዊሃ ቃለ-መሃላ ፈፀመ – George Wiha Made a Vow

                                                

የቀድሞው ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ሆኖ ቃለ መሃላ ፈፀመ።

ዊሃ ሞንሮቪያ ውስጥ ቃለ መሃላውን በፈፀመበት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለተሰበሰበው ሕዝብ ባደረገው ንግግር ”ለበርካታ ጊዜያት ስታዲየም ውስጥ ተገኝቻለው፤ ዛሬው ግን ከሌሎቹ ጊዜያት እጅግ የተለየነው” ብሏል።

ከአውሮፓውያኑ 1944 ወዲህ ላይቤሪያ ውስጥ በዲሞክራሲያዊ መንገድ በተደረገ ምርጫ የስልጣን ሽግግር ሲደረግ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ

ፕሬዝዳንት ዊሃ ስልጣን ያስረከቡትን ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ለዓመታት ከዘለቀ የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ ለሃገሪቱ ሰላም በማምጣታቸው ምስጋናውን አቅርቧል።

በቃለ መሃላው ሥነ-ሥርዓት ወቅት ባደረገው ንግግር ሃገሪቱ ላሉባት ችግሮች ”ፈጣን መፍትሄ” አመጣለሁ ብሎ ቃል ለመግባት እንደማይችል፤ ነገር ግን ላይቤሪያዊያን ወደሚያልሟቸው ግቦች ለመድረስ ፈጣን እርምጃዎችን እንደሚወስድ ዊሃ ተናግሯል።

ጨምሮም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ትልልቅ ጉዳዮች መካከል ሙስናን መዋጋትና የመንግሥት ሰራተኞች ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ ማድረግ እንዲሁም ለግሉ ዘርፍ ላይቤሪያ በሯ ክፍት መሆኑን ማሳየት እንደሆነ ተናግሯል።

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement