ቬንዙዌላ ባጋጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ወደ ኮሎምቢያ የተሰደዱ ዜጎቿ ቁጥር ከ550ሺህ በላይ ደርሷል – Venezuela Migrants has Surpassed 550 Thousand People as a Result of its Economic Crisis.

                                                              

በላፉት ስድስት ወራት ብቻ በሀገሪቱ በተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ በኮሎምቢያ የሚኖሩ ቬንዚዌላዊያን ቁጥር ስልሳ ሁለት በመቶ ጨምሯል፡፡

የሀገሪቱ የስደተኞች ባለስልጣናት እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት ብቻ 550 ሺህ ቬዚዌላዊያን ኮሎምቢያ ወስጥ ይኖራሉ፡፡

ከዚህ ወስጥም አብዛኞቹ ህገ ወጥ ናቸው፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ይህን እያደረገ ያለው በተለይም በጠረፍ አካባቢ ለስደተኞች የምግብ, የመጠለያና የጤና ክብካቤ ለመስጠት ነው፡፡

ባለስልጣናቱ እንደሚሉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቬዚዌላዊያን መሰረታዊ የምግብ አቅርቦት ችግር ስላጋጠማቸው በሀገረ ኮሎምቢያ የስደተኞች መለያ ካርድን ተመዝግበው በመውስድ በድንበር አቅራቢያ ወደ ሀገሪቱ በመምጣት በቀላሉ እንዲሸምቱ ተደርገዋል፡፡

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታም በኮሎምቢያ ከሚኖሩ ቬንዚዌላዊያን ውስጥ 126 ሺህ የሚሆኑት ህጋዊ ፍቃድ አጊኝተው በሀገሪቱ እንዲቆዮ ተደርጓል፡፡

ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ኮሎምቢያ ለስደተኞች እያደረገች ባለችው ድጋፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ ሀገሪቱ እርዳታ እንደሚልክ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement