የከተራ በዓል ዛሬ ይከበራል – Today “Ketera” Festival Will be Celebrated

                                                                            

የከተራ በዓል በመላ ሀገሪቱ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ በድምቀት ይከበራል።

በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ምዕመናን፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች እና በርካታ ጎብኝዎች በተገኙበት በጃን ሜዳ ይከበራል።

ከሰዓት በኋላም የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ መዘምራን፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስትና ምእመናን የተለያዩ መንፈሳዊ ዝማሬዎችን እያቀረቡ ታቦታቱ አዳራቸውን ወደሚያደርጉበት ጃን ሜዳ ያመራሉ።

በነገው እለትም የጥምቀት በዓል በምዕመኑ ዘንድ በድምቀት የሚከበር ይሆናል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሃንስ እጅ ለመጠመቅ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ የወረደበትን እለት ለማሰብ የሚከበር ነው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement