ሳምሰንግ ተጣጣፊ አዲስ የስልክ ዓይነቱን በ2019 ይፋ እንደሚያደርግ ገለፀ – Samsung Reviles to Release Folding Smartphone in 2019

                                               

ሳምሰንግ ኤሌክትሮኒክስ ኩባንያ በአውሮፓውያኑ 2019 ተጣጣፊ ስማርት የሞባይል ስልክን ይፋ እንደሚያደርግ ገለፀ።

ኩባንያው የሚተጣጠፍ የመመልከቻ ስክሪን ያለው ይህ ስልክ ይፋ ይደረጋል ከተባለ ረዥም ጊዜ አስቆጥሯል።

በተለይም ከተጠቃሚዎች ዘንድ ያለ ፍላጎት ይህን አዲስ የስልክ ሞዴል ይፋ ማድረጊያ ጊዜን እንዳራዘመው ነው ኩባንያው የጠቆመው።

samsung_folding2_15012018.jpg

ሆኖም በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ላይ ስልኩን ወደ ማምረት እንደሚገባ ነው ኩባንያው ያስታወቀው።

ኩባንያው ሊሰራ ያቀደውን ስማርት ስልክ ለተመረጡ ደንበኞቹም በ2018 ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement