ሶማሊላንድ አስገድዶ መድፈርን በተመለከተ የመጀመሪያ ሕግ አወጣች – Somaliland Passes First Law Against Rape

                                                            

ሶማሊላንድ ከተመሠረተች ለመጀመሪያ ጊዜ አስገድዶ መደፈርን የሚያወግዝ ሕግ አርቅቃለች።

በቀደመው ጊዜ አስገድዶ መድፈር የፈፀመ ግለሰብ ቢበዛ በደል የፈፀመባትን ሴት ማግባት ይኖርበታል እንጂ በሕግ አይጠየቅም ነበር።

አዲስ የወጣው ሕግ ግን አስገድዶ የመድፈር ወንጀል የፈፀመ ሰው እስከ 30 ዓመት የሚደርስ የእሥራት ቅጣት ሊበይንበት ይችላል።

በፈረንጆቹ 1991 ነበር ሶማሊላንድ እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር ከሶማሊያ ራሷን ነፃ ብታደርግም፤ በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ዘንድ እውቅ አላገኘችም።

የሃገሪቱ ፓርላማ አፈ-ጉባዔ ባሼ ሞሐመድ ፋራህ ለቢቢሲ ሲናገሩ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ አየተባባሰ በመምጣቱ ሕጉ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

“አሁን አሁን እስከ ሰባት የሚደርሱ ሰዎች አንዲት ሴት ላይ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል እየፈፀሙ ይገኛሉ። አዲስ የወጣው ሕግ ወንጀሉን ሙሉ በሙሉ ያስወግድልናል ብለን እናምናለን” ብለዋል።

ሕጉ የሕፃናትና ሴቶች መብት ተሟጋቾችን ዓመታት የዘለቀ ጉትጎታ ተከትሎ የመጣ ነው።

የሴቶች አጀንዳ ከተሰኘ ተቋም የመጣችው ፋይሳ አሊ ዩሱፍ ለቢቢሲ እንተናገረችው የሕጉን መውጣት ለዘመናት በጉጉት ሲጠብቁት የነበረ ጉዳይ ነው።

የሕጉ ተግባራዊ መሆን ሶማሊላንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት እንደሚጨምረው ይጠበቃል ስትል የቢቢሲዋ አን ሶይ ዘግባለች።

 

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement