ከተሰበረ ራሱን የሚጠግን የስማርት ስልክ መስታወት ተሰራ – Self-healing Smashed Phone Screen

                                                                        

ዚህ በኋላ ስክሪናቸው የተሰባበረ የስማርት ስልክ ስክሪን መያዝ ሊቀር ነው ይለናል ከወደ ጃፓን የገኘ መረጃ።              

ምክንያቱ ደግሞ ራሱን በራሱ ወደ ነበረበት መልሶ የሚጠግን መስታወት የጃፓን ቶክዮ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በመስራታቸው ነው ተብሏል።

የጃፓን ተመራማሪዎች አዲስ አይነት መስታወት መስራታቸውን ያስታወቁ ሲሆን፥ ይህም ወድቆ ቢሰነጠቅም ይሁን ቢሰበር ወደ ነበረበት መልሶ ራሱን የሚጠግን ነው።

መስታወቱ ፖለይመር ከተባለ ሴንቴቲክ ፕላስቲክ ንጥረ ነገሮች የተሰራ ሲሆን፥ በሚሰበርበት ጊዜ ማሞቅ እና ማቅለጥ ሳያስፈልገን በእጃችን ብቻ አንድ ላይ እንዲያያዝ ስንገፋው ይጣበቃል።

በቶክዮ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድኑ መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ታኩዞ አይዳ፥ ራሱን በራሱ የሚጠግነው መስታወት ለስማርት ስልኮች ስክሪንነት በስፋት ጥቅም ላይ እንደሚውል ተስፋ አለን ብለዋል።

እንዲህ አይነት መስታወት መሰራቱ ስማርት ስልኮችም ይሁን ሌሎች መገልገያዎች በስክሪናቸው አማካኝነት ለረጀም ጊዜ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የሚያደርገውን ችግር ይቀርፋልም ብለዋል።

ከዚህ በፊት ራሱን በራሲ የሚጠገን ፕላስቲክ ስክሪን መሰራቱን የገለፁት የጥናቱ ተመራማሪዎች፥ ይሄኛው ግን ጥንካሬ ካለው ንጥረነገሮች ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራ መስታወት ነው ብለዋል።

የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎችም ከዚህ ቀደም ባካሄዱት ምርምር ፖለይመርን በመጠቀም ከመደበኛ መጠኑ እስከ 50 በመቶ ድረስ መለጠጥ የሚችል እና ከተሰበረም በ24 2ዓት ውስጥ ራሱን ወደ ነበረበት መልሶ የሚጠግን መስታወት መስራታቸው ይታወሳል።

ኤል ጂ የተባለው የስማርት ስልክ አምራች ኩባንያ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 ባመረተው “ጂ ፍሌክስ 2” ስማርት ስልኩ ላይ ይህን ስክሪን ተጠቅሞ ነበር ተብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement