የአፍ መድረቅ ችግሮች ምክንያቶችና መፍትሄዎቻችው – Dry Mouth (Xerostomia)

                                                       

የአፍ መድረቅ ችግር የሚከሰተው በአፋችን ውስጥ የሚገኙ ምራቅ (saliva) አመንጪ እጢዎች (salivary glands) ምራቅን በበቂ ሁኔታ ማመንጨት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት ነው።

ምራቃችን በ አፋችን ውስጥ በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት የጥርስ መቦርቦር እንዳይፋጠር የሚረዳ ሁኔታን ያስመቻቻል። ከዚህም በተጨማሪ ምግብን አላምጦ የመዋጥ ሂደትን እንድናደርግና ለምግብ መፈጨት ሂደት የሚያስፋልጉ ኢንዛይምስ የማመንጨት ተግባርን ያስከናውናል።
የምራቅ መመንጨት በሚቀንስ ጊዜ የ አፍ መድረቅ ይከሰትና ጤናችንን ሊያስቃውስ ይችላል።
የአፍ መድረቅ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
* አፋችን ውስጥ የማጣበቅ ስሜት ሲሰማን
*መጥፎ የአፍ ጠረን
*ለማላመጥ ፣ ለመዋጥ እና ለመናገር መቸገር
*የጉሮሮ መሻከር ወይንም ቁስለት
*የምግብ ጣዕም ማጣት ናቸው።

የአፍ መድረቅ የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
-: የአፍ መድረቅ የሚመጣው ምራቅ አመንጪ እጢዎች በሚፈለገው መጠን ምራቅን ማመንጨት ሲያቆሙ ነው ለዚህም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ሁኔታዎችን እናያለን።
* መድሃኒቶች
አብዛኛዎቹ መድሀኒቶች የአፍ መድረቅ የጎንዮሽ ጉዳታቸው እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ። ለምሳሌ ለደም ግፊት፣ለመደበት፣ጭንቀት እና አንዳንድ የአለርጂ መድሀኒቶች ይጠቀሳሉ።
*እድሜ
እድሜአችን በጨመረ ቁጥር የተለያዩ አካላዊ ለውጦችን ተከትሎ የ አፍ መድረቅም የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው።
*የነርቭ ጉዳት
በጭንቅላት እና አንገት አካባቢ የሚገኙ ነርቮች በሚጎዱ ጊዜ የአፍ መድረቅ በተያያዥነት ሊመጣ ይችላል።
*ሲጋራ ማጤስ፣ የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መውሰድና ሌሎች አደንዛዥ እፆችን መጠቀም የአፍ መድረቅን ያስከትላል።
*ኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ 
ካንሰርን ለማከም የሚሰጡ ህክምናዎች የ አፍ መድረቅን ለጊዜያዊ ወይንም በቋሚነት ሊያስከትሉ ይችላል።
*ሌሎች የጤና ችግሮች ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ፣የስኳር ህመም፣ስትሮክ፣የፈንገስ ኢንፌክሽን ህመሞች ለአፍ መድረቅ ችግር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
*ማንኮራፋትና አፍን ከፍቶ መተንፈስ ሌሎች መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።
ከአፍ መድረቅ ጋር በተያያዘ የሚመጡ ሌሎች ችግሮች ምንድን ናቸው?
* የጥርስ መቦርቦር እና የድድ ህመም
*የከንፈር ቁስለት
*የፈንገስ ኢንፌክሽን
*የከንፈር መሰነጣጠቅ
*የክብደት መጠን መቀነስ ናቸው።
አንድ ሰው የአፍ መድረቅ ሲያጋጥመው ወደ ሀኪም በመሄድ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል። 

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement