ምጥ መጀመሩን እንዴት ማወቅ እንችላለን? – How to Know That it is Time for Labor?

                                                            

How to Know That it is Time for Labour?

ምጥ የሚጀምርበት ጊዜ ወይም ጀምሮ እንደሆነ ለማወቅ አንዳንዴ ሊያስቸግር ይችላል። ለመድረሱ ምልክት ግን የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ።

. ጽንሱ ወደ ወገብ አጥንቶች መሃል ዘልቆ መግባት
. የማህጸን ፈሳሽ መጨመር
. ለመጀመርያ ጊዜ ከማህጸን ንጹህ ወይም ደም የቀላቀለ እንደ ልፋጭ አይነት ፈሳሽ መውጣት
. የማህጸን ጭብጥ ዘርጋ ማለት(ምጥ) እያየለ መምጣት
.የእንሽርት ውሃ መፍሰስ

በምጥ ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉ የአደገኛ ሁኔታዎች ምልክቶች ምንድን ናቸዉ?
ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ ።
. የእንሽርት ውሃ ቢፈስም ምጥ ግን አለመጀመር
.በምጥ ሰአት የጽንሱ አቀማመጥ ትክክል አለመሆን
.ከወሊድ በፊት ደም ከማህጸን መፍሰስ ሲጀምር
.ምጥ ለብዙ ጊዜ ሲቆይ
.አረንጓዴ ወይም ቡናማ የእንሽርት ውሃ የፈሰሰ እንደሆነ
.ትኩሳት ሲጀምር እና የእንሽርት ውሃ መጥፎ ሽታ ሲኖረው
.እንደሚጥል በሽታ አይነት ማንቀጥቀጥ እና ራስ መሳትን ሲጀምር
. የህጻኑ እትብት ቀድሞ በብልት በኩል ከታየ ናቸው

እነዚህ ምልክቶች የታዩባት ነፍስጡር ሴት ባስቸኳይ ሐኪም ቤት መሄድ ይኖባታል።

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement