NEWS: አሜሪካ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ ጠየቀች – North Korea: US Urges all Nations to Cut Ties

                                                            

አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ያደረገችውን የባሌስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ተከትሎ የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ከሀገሪቱ ጋር ያላቸውን የንግድና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲያቋርጡ ጥሪ አቀረበች።

                   

በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ኒኪ ሐሌይ እንዳሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለቻይና አቻቸው ለፒዮንግያንግ የሚያቀርቡትን ነዳጅ እንዲያቋርጡ ጠይቀዋል።

አሜሪካ ግጭትን አትፈልግም ነገር ግን ሰሜን ኮሪያ መንግስት ጦርነት ከተጀመረ “በማያዳግም መልኩ ይደመሰሳል” ብለዋል።

ይህ ማስጠንቀቂያ የመጣው ሰሜን ኮሪያ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ የሚሳኤል ሙከራዋን ማድረጓን ተከትሎ ነው።

ሰሜን ኮሪያ ባለፈው እሮብ ያደረገችው የሚሳኤል ሙከራ 4475 ኪሎ ሜትር ከፍ ብሎ የሚወነጨፍ እና ከአለም አቀፉ የጠረፍ ጣቢያ በላይ የሚበልጥ እንዲሁም ቦንብ ተሸክሞ የመሬትን አካል ሰንጥቆ መግባት የሚችል ነው ስትል ገልፃለች።

የዚህን መግለጫ እውነታነት በማንም ወገን ያልተረጋገጠ ሲሆን የመስኩ ባለሙያዎችም ሀገሪቷ ይህን አይነት ቴክኖሎጂ ይኖራታል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል።

የሰሜን ኮሪያ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኪም ጆንግ ኡን የሚሳኤል ማስወንጨፍ ሙከራውን “ወደር የማይገኝለት”ና “አስደናቂ” ሲሉ አሞካሽተውታል።                                                                                     

አጭር የምስል መግለጫሰሜን ኮሪያውያን የሚሳኤል ማስወንጨፍ ሙከራ መደረጉን አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን ሲገልፁ

በዚህ አመት ከተደረጉት ሙከራዎች በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ውግዘት የደረሰበት እና የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂድ ያደረገ ነበር።

ሚስ ሐሌይ ሲያስጠነቅቁም “ቀጣይነት ያለው ፀብ አጫሪነት” ወደፊት አካባቢውን ወደ አለመረጋጋት ይወስደዋል ብለዋል።

በተባበሩት መንግስታት የሩሲያ አምባሳደር ቫስሊ ኔቤንዚያ ደግሞ ፒዮንግ ያንግ የሚሳኤል እና የኒኩሌይር ሙከራዋን ማቆም አለባት፣ ዋሽንግተንም ብትሆን ከደቡብ ኮሪያ ጋር በመጪው ታህሳስ ለማድረግ ያቀደችው ወታደራዊ ልምምድ ” አሁን ያለውን ያልተረጋጋ ሁኔታ ወደባሰ ደረጃ ይወስደዋል።” ብለዋል።

ቻይናም በበኩሏ ሰሜን ኮሪያ ሙከራዎቿን በሌላ በኩል ደግሞ አሜሪካም ወታደራዊ ልምምዷን ማቆም እንዳለባቸው ሐሳብ ሰጥተዋል፤ ይህንን ደግሞ ከዚህ በፊት ዋሽንግተን እንደማትስማማበት ይፋ አድርጋለች።

የነዳጅ ዘይቱን መስመር ማቋረጥ

“ቻይና የበለጠ ነገር እንድታደርግ እንፈልጋለን።” ብለዋል ሚስ ሐሌይ። “ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለፕሬዚዳንት ዢ ዛሬ ጠዋት ደውለው ቻይና ለሰሜን ኮሪያ የምትሸጠውን የነዳጅ ዘይት ማቋረጥ አለባት ወደሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል።”

“የኑክሌር ማብላያው ዋነኛ አንቀሳቃሽ ነዳጅ መሆኑን እናውቃለን።” ብለዋል። “ዋነኛ የነዳጅ አቅራቢዋ ደግሞ ቻይና ነች።”

ቻይና የሰሜን ኮሪያ ዋነኛ ወዳጅና የንግድ አጋር ስትሆን ፒዮንግ ያንግ ለነዳጅ አቅርቦቷ የቻይና ጥገኛ ነች።

እሮብ እለት ቀደም ብሎ ዋይት ሐውስ ሚስተር ትራምፕ ከኢ ጂንፒንግ ጋር በስልክ ማውራታቸውንና “ሰሜን ኮሪያ ፀብ አጫሪነቷን እንድትተው የኒክሌር ምርቷንም እንድታቆም ያላቸውን አቅም ሁሉ ተጠቅመው እንዲያሳምኑ ጠይቀዋቸዋል።” ብሏል።

 

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement