ውቅያኖስን እንታደግ በሚል መፈክር ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በአሸዋ ላይ በመወዳደራቸው በድንቃድንቅ መዝገብ ሰፍረዋል – Thousands Take Part in Record-breaking Beach Race to Help “save the ocean”

                                                            

ውቅያኖስ እንታደግ በሚል መፈክር ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች በአሸዋ ላይ በመወዳደራቸው በዓለም የድንቃድንቅ መዝገብ ሰፍረዋል።

መሰረቱን ካሊፎርኒያ ያደረገው “ሰርፊንግ ማዶና ኦሺንስ ፕሮጀክት” ድርጅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በባህር ዳርቻ በአሸዋ ላይ ሩጫ በማወዳደር የዓለም ግዙፉን የአሸዋ ላይ ውድድር ያዘጋጀ በሚል ተመዝግቧል።

ድርጅቱ ለየት ያለውን ውድድር ያዘጋጀው ውቅያኖስን እንጠብቅ እንታደግ የሚል ንቅናቄን ለመፍጠር ነው ተብሏል።

                                                                                           

ውድድሩ በሳንዲያጎ በውቧ ኢንቺኒታስ የባህር ዳርቻ የተካሄደ ሲሆን፥ 4 ሺህ 288 ሰዎችን የመለማመጃ ጫማቸውን ተጫምተው እንዲሮጡ በማድረግ ነው በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ የሰፈሩት።

የተወሰኑ ተወዳዳሪዎች ራሳቸውን ፎቶ ለማንሳት ሲሉ ለአፍታ ውድድሩን በማቆማቸው በድንቃድንቅ መዝገብ ስማቸው ሳይሰፍር ቀርቷል።

ሆኖም በድንቃድንቅ መዝገቡ ላይ ለመስፈር በትንሹ 1 ሺህ ሰዎችን ማሳተፍ ያስፈልግ የነበረ ሲሆን፥ ከዚያ በላይ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ውድድሩን በማጠናቀቃቸው ለድሉ በቅተዋል።

                                                       

ተሳታፊዎቹ በአሸዋ ላይ በትንሹ 100 ሜትሮችን መሮጥ የሚጠበቅናቸው ቢሆንም የሰርፊንግ ማዶና ኦሺንስ ፕሮጀክት ድርጅት ግን ለአዋቂዎች በ5 ሺህ በ10 ሺህ እና በ15 ሺህ ኪሎ ሜትር የተለያየ የርቀት ሩጫን በግዴታ አስቀምጧል።

ለታዳጊዎች ደግሞ 1 ሺህ ሜትርን መሮጥ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

በዚህም በርካቶች የተጣለባቸውን ነየርቀት ወሰን በአሸዋ ላይ ሩጠው ጨርሰዋል።

ምንጭ፦ www.guinnessworldrecords.com

Advertisement