ትራምፕ ሰሜን ኮሪያ ሽብርተኝነትን ትደግፋለች ብለዋል – Donald Trump Declares North Korea a State Sponsor of Terrorism

                                                                                         

ሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሜን ኮሪያ ሽብርተኝነትን የምትደገፍ ሃገር በመሆኗ “የሽብርተኝነት አጋር” ልትባል ይገባል ብለዋል።

ሃገሪቱ ሽብርተኝነት ከሚደግፉ ሃገራት ዝርዝር ላይ ስሟ ከተፋቀ ዘጠኝ ዓመታት ተቆጠርዋል።

በፓርቲያቸው ካቢኔ ስብሰባ ላይ የተገኙት ትራምፕ ሰሜን ኮሪያ ላይ የሚጣሉ ሌሎች ማዕቀቦችን በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ይፋ እንሚያደርጉም ተናግረዋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴይለርሰን ግን የቅጣቶቹ ተግባራዊነት ላይ ውስንነት ሊኖር እንደሚችል አይካድም ብለዋል።

ትራምፕ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር መሣሪያ ግንባታ ወቅሰው ሃገሪቱ ለሽብርተኝነት እያደረግች ያለው ድጋፍም ሊኮነን ይገባዋል ብለዋል።

ሰሜን ኮሪያ ሽብርተኝነት የሚደግፉ ሃገራት ዝርዝር ውስጥ የማካተት ሂደቱ ዘግይቷል ብለዋል።

ወርሃ መስከረም ላይ አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ላይ ሊጣሉ ይገባል ያለቻቸውን የቅጣት ሃሳቦች ለተባበሩት መንግሥታት አቅርባ የተወሰኑት መፅደቃቸው አይዘነጋም።

የኪም ጆንግ-ኡን ንብረት እንዳይንቀሳቀስ እንዲሁም የነዳጅ ወጭና ገቢ ንግድ ላይ ገደብ እንዲጣል የሚያዘው ማዕቀብ ተግባራዊ መሆኑም ይታወሳል።

                                                                                           

ሰሜን ኮሪያ ሽብርተኝነት የምትደግፍ ሃገር ተብላ ተፈርጃ የነበረ ቢሆንም ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በጆርጅ ቡሽ ዘመን ከዝርዝሩ እንድትፋቅ ተደርጋ ነበር።

የትራምፕ መንግሥት ሰሜን ኮሪያ ላይ ቅጣት እንዲጠናከር ጠንክሮ እየሠራ ቢሆንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሬክስ ቴይለርሰን ግን አሁንም ዲፕሎማሲ ዋነኛው አማራጫችን ነው ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ነገር ግን ሰሜን ኮሪያ የሽብርተኝነት አጋር ተብላ መሰየሟ ዲፕሎማሲያዊ ሂደቶችን እንደሚያጓትት የቢቢሲዋ ባርባራ ፕሌት ትናገራለች፤ በሚሳኤል ሙከራ ሰሜን ኮሪያ አፀፋውን ልትመልስ እንደምትችል በመገመት።

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement