ቢቢሲ አፍሪካ በአህጉሪቱ የተሻለ የሚዘወተሩና ምርጥ ምግቦችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል – African cuisines.

                                                                             

በአህጉሪቱ ከ50 በላይ ተወዳጅ ምግቦችን ባካተተው ምግብ ዝርዝር የመጨረሻ ያላቸውን አምስት ተወዳጅና ተመራጭ የምግብ ዝርዝሮች ለይቶ አውጥቷል።

በዚህ ዝርዝር ታዲያ የእኛው ኢትዮጵያዊ ምግብ በየአይነቱ ከአምስቱ ተመራጭ ምግቦች ተካቶ የመጨረሻዎቹ ዝርዝር ውስጥ መግባት ችሏል።

ተለይተው የተመረጡ ምግቦች ዝርዝር፤

1.ንዶሌ እና ፕላንቴንስ – ካሜሩን፦ ከስጋ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ስራስር እና ዱቄት የሚዘጋጅ ነው።

                                                              

ራሱን ችሎ የሚበላ አልያም ማባያ የሚሆንና ከተለያዩ ምግቦች ጋር ተቀላቅሎ መዘጋጀት የሚችል የካሜሩናውያን ተወዳጅ ምግብ መሆኑም ይነገራል።

2.በየአይነቱ – ኢትዮጵያ፦ ይህን ኢትዮጵያዊ የሆነ የሚያውቀው በብዛት በፆም ወቅት የሚዘወተር ምግብ ነው።

                                                             

3.ካልዴይራዴ ደ ካብሪቶ – አንጎላ እና ሞዛምቢክ፦ ይህ ደግሞ በሾርባና ሚኒስትሮኒ፣ በሳንድዊች እንዲሁም ከተለያዩ ምግቦች ጋር መመገብ በሚያስችል መልኩ ለገበታ የሚቀርብ ነው።

                                                             

ከአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንቁላል፣ ስጋና የስጋ ተዋጽኦ እንዲሁም ከተለያዩ ስራስሮች የሚዘጋጅ የሃገሬው ሰዎች ተወዳጅ ምገብ ነው።

4.ሱያ – ናይጀሪያ፣ ኒጀር፣ ጋና እና ካሜሩን፦ በምዕራብ አፍሪካ ሃገራት የሚዘወተርና ከተጠበሰ ስጋ የሚዘጋጅ ሲሆን ከአትክልትና እንደ ድንች ካሉ ስራስሮች ጋር ተቀላቅሎ የሚቀርብ ነው።

                                                             

የበሬ አልያም የፍየል ስጋ በጥቂቱ ተቆራርጦና ረዘም ባለ መጥበሻ እንጨት ተሰክቶ ከተጠበሰ በኋላ ይቀርባል።

አልያም ከዶሮ የሚዘጋጅ የዚህ ምግብ ጥብስም አለ። 

5.ሮማዛቫ – ማዳጋስካር፦ ከአይብ፣ ስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ በሾርባና ከተለያዩ ምግቦች ጋር ለመመገብ በሚያመች መልኩ የሚዘጋጅ ምግብ ነው።

                                                                

ይህ ምግብ ከሾርባ በተጨማሪ ከሩዝና ከዳቦ ጋር መመገብ በሚያስችል መልኩ የሚዘጋጅ ሲሆን፥ በሃገሬው ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ምግብ መሆኑ ይነገራል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

Advertisement