በኦሎምፒክ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪው ሮቤል – Robel Teklemariam, Ethiopia’s First Ever Ice Skater

                                                           

ሮቤል ተክለማርያም እባላለሁ የምኖረው ከጃፓን ዋና ከትማ ቶኪዮ የአራት ስዓት መንገድ ርቀት ላይ በምትገኘው ናጋኖ በምትባል ከትማ ውስጥ ነው።

እዚህ የበረዶ ሸርተቴ (አልፓይን ስኪንግ) አስትምራለሁ ትምህርት ቤቱንም በበላይነት የምቆጣጠረው እኔ ነኝ።

ለመጅምሪያ ጊዜ ወደዚህ ሃገር የመጣሁት ከአስር ዓመታት በፊት ሲሆን ጠቅልዬ ከመጣሁ ደግሞ ሶስት ዓመታትን አስቆጠርኩ።

አሜሪካ በነበርኩበት ወቅት ሜይድ ክለብ የሚባል የፈረንሳይ ድርጅት ውስጥ የበረዶ ሸርተቴ አስተምር ነበር። በተጨማሪም ስፖኔስሮቼም ነበሩ። ለድርጅቱም በኢንዶኔዥያ፣ አውስትራሊያ፣ ቱርክ፣ ቱኒዝያ፣ ታይላንድ እና ቻይና ውስጥ ስርቻለሁ።

ከኦሎምፒክ ውድድሬ በኃላ ኢትዮጵያ ውስጥ ጃፓን ለሚደረግ ውድድር ዝግጅት እያድረግኩ ሳለ አሜሪካ መጥቼ እንዳስተምር ጠየቁኝ። ውድድሩ ላይ ብቻ ማተኮር እንድምፈልግ ስነግራቸው ጃፓንም የበረዶ ሸርተቴ ማስተማሪያ እንዳላቸው ሳውቅ በክረምት ለማስተማር መጣሁ።

ከበረዷማው ኮሎራዶ ብመጣም የጃፓን የበረዶው ጥራትም ሆነ ብዛት በጣም ነው ያስደነቀኝ።

በዓለም ምርጥ በረዶ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ነው።

የተወለድኩት አዲስ አበባ ሲሆን እስከ ሶስትኛ ክፍልም የተማርኩት ቅዱስ ዮሴፍ የወንዶች ትምህርት ቤት ነው ።

በጊዜው ከደርግ መንሥስት ጋር ተያይዞ በነበረው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እናቴ ወደ ኒው ዮርክ የተባበሩት መንግስታት ቢሮ ተዛወረች።

በኒው ዮርክ የባህል ግጭት ነው የደረሰብኝ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ህፃን ልጅ ሲያድግ ውጭ ተጫውቶ፤ ተንቦጫርቆ ነው የሚያድገው።

የኒው ዮርክ ኑሮ አንድ አፓርትመንት ውስጥ ትቆልፎ መዋል ነው። ከዚያ በላይ እንግሊዝኛ ቋንቋ አለመቻሌ ሁኔታውን አከበደብኝ።

የመጀመሪያ ትምህርት ቤት የሄድኩባት ቀን በህይወቴ መጥፎ ከምላቸው ቀናቶች አንዷ ናት።

አስታውሳለሁ የጥዋቱን ክፍለጊዜ ከተማርን በኋላ ለምሳ ወጣን። ልጆቹ ሲያዋሩኝ የምመልሰው በአማርኛ ነበር።

ሰምተውት የማያውቁት ቋንቋ በመሆኑ ሁሉም መሳቅ ጀመሩ።ተሳቅቄም እያለቀስኩ ከትምህርት ቤት ወጥቼ መንገዱን ባላውቅዉም እግሬ ወዳመራኝ ሄድኩ።

በህይወቴ የማልረሳት ሴትም ያጋጠመችኝ በዚሁ አጋጣሚ ነበር። ሁኔታዬ ግራ ቢያጋባት ልትረዳኝ መኪና ውስጥ አስገባችኝ።

እዬሄድንም እያለ እንደ እድል ሆኖ የምኖርበትን ህንፃ ሳየው ጠቆምኩዋት።

የህንፃው አከራይ እንዳየኝ አወቀኝ። ከዚያ ደግሞ ሌላ ጭንቀት፤ ለምን ትምህርት ጠፍቼ እንደመጣሁ በውቅቱ ቤት ለነበረችው አክስቴ ምን ብዬ ልመልስ።

እናም የዶሮ አጥንት አንቆኝ ነው አልኩ እምቡላንስ ተጠራ እናቴም ተጠራች።

ባጭሩ እዛ ትምህርት ቤት ተመልሼ አልሄድኩም።

በአማራጩ እንግሊዝኛ ቋንቋ እንዳሻሽል በግል ቋንቋ የሚያስተምሩ እስተማሪ ጋር ተላኩ። ከዚያም ሌክ ፕላሲድ የሚባል አዳሪ ትምህርት ቤት ገባሁ።

እንግዲህ በዚሁ አጋጣሚ ነው የበረዶ ሸርተቴ ስፖርትም ጋር የተዋወቅኩት። ገና እንዳየሁት ነው በፍቅር የተለከፍኩት። የበረዶ ሸርተቴ ውድድርንም ጀመርኩ። በሀገር አቀፍ የተለያዪ ውድድሮችም ላይ መሳተፍ ጀመርኩ።

ዪኒቨርስቲም በዛው ቀጠልኩብት። የአትሌቲክስ የትምህርት እድል በማግኘቴ በበረዶ ሸርተቴ አሉ ከሚባሉት ከአስሩ ዪኒቨርስቲዎች በአንዱ ነው።

ለኢትዮጵያ መወዳደር ያሰብኩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበርኩበት ወቅት ነው።

                                                                   

በምወዳደርበት ወቅት ከየት ነው የመጣው የሚሉ ጥያቄዎች ለአሰልጣኜ ይውረውወርልለት ጀመር። ከኢትዮጵያ ነው ሲላቸው አንደኛው በቀልድ መልኩ ለኢትዮጵያ ቢወዳደር የሚል አስተያየት ሰጠ። ለኔ ግን ቀልድ አልነበረም።

በዛን ወቅት ስለ አበበ ቢቂላ እንዲሁም ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ እየተማርኩ የነበረበት ጊዜ ነው። ነግር ግን እንዴት ኢትዮጵያን መወከል እንደምችል ባጠያይቅም መልስ የሚሰጠኝ አጣሁ።

ከዩኒቨርስቲ በኃላ የኬንያ የበረዶ ሸርተቴ ተወዳዳሪዎችን ሳይ እንደገና ለኢትዮጵያ መወዳደር እንዳለብኝ ወስንኩ። በውቅቱም በስፖርቱ ከፍትኛ ደረጃ የደረስኩብት ጊዜ ነበር።

ሳጠያይቅም ከዓለም የበረዶ ሸርተቴ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እውቅና ያለው የበረዶ ሸርተቴ ማህበር እንደሚያስፈልገኝ ነገሩኝ።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴን እንዲሁም የስፖርትና የወጣቶች ሚኒስትርን መወዳድር እንድምፈልግ ነገርኩዋችው።

ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጀምሮ የነበረው ምላሽ ቀና ቢሆንም የበረዶ ሸርተቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ባልመኖሩ እንደ አዲስ ፌዴሬሽን ማቋቋሙ ብዙ እመታትን ፈጀ። የኦሎምፒክ ውጤቴ ጥሩ እልነበረም ለኔ ግን ዋናው ነገር ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የማትታወቅበት ስፖርት መወከሉ ነበር።

ይህ እጋጣሚም ከ 22 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሬ የመመለስን አጋጣሚን ፈጥሮልኛል። ብዙ ዓመት ርቄ ስለቆየሁ ከህዝቡ ጋር ለመግባባት ይከብደኛል የሚል ፍራቻ ነበረኝ። በተቃራኒው ከአሜሪካ በበለጠ የሃገር ስሜት የትሰማኝ ኢትዮጵያ ነው። ወደ ኢትዮጵያ ብመላለስም አሁን ቋሚ መኖሪያዬ ጃፓን ናት።

ጃፓንና ኢትዮጵያ በባህል በጣም የሚመሳሰሉ ህዝቦች ናችው። ለስዎች ያላቸው ከበሬታ፣ ስላምታ ሲያቀርቡ ጎንበስ የሚሉበት መንገድ እንዲሁም የሻይ አፈላል ስርዓታችው ከኛ ቡና ጋር ተመሳሳይ ነው።

ጃፓን የምትመች ሃገር ናት። የምኖርበት ከተማ በተራራና በህይቅ የተከበበች ናት። በተለያዩ ወቅቶችም መልክአምድሩ መለያየቱ ስፍራው የልብ እርካታን ይሰጣል።

                                                                 

ይህ ቦታም ልጄን ልያን ያፈራሁብት ስለሆነ ልዩ ትርጉም አለው። ከልያ በተጨማሪ የእንጅራ ልጀም ሌላ ስጦታዬ ናት።

ምግባቸውንም በጣም ነው የምወደው በተለይም ከሩዝና ጥሬ አሳ የሚሰራው ሱሺ እንዲሁም ከአትክልትና ስጋ የሚሰራው ያኩኒኩ የኔ ምርጫ ናቸው።

ጃፓን በስርዓት የትሞላች፤ ሁሉ ነገር የደራጀች ሀገር ናት። ከኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከዓለም የሚለያት የሚገርም የስራ ባህላቸው ነው። ከ30 ሃገራት በላይ ሃገራትን አይቻለሁ ይሁን እንጂ እንደዚህ አይነት የስራ ባህል አስተውዬ አላውቅም።

ከዚህ በተጨማሪ ለጊዜ የሚሰጡት ትኩረት ያስደንቃል። ስከንዶች ትርጉም አላችው። ለምሳሌ አውቶብሱ ይመጣል ከተባለበት ሰከንድ አታልፍም።

ቋንቋውን ብለምደውም ማንበብና መፃፍ ክብዶኛል። ከፊደሎቻቸው በተጨማሪ ከ 20ሺ በላይ ካንጅ የሚባል የቻይናን ምልክት ይጠቀማሉ።

ሁሌም ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች። የጥዋት ፀሀይ እንዲሁም ምግቡ በትለይ ክትፎ፤ የእህቴ ቤት ምግብ በዓይኔ ይዞራል።

ካለሁብት ከተማ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ሩቅ ስለሆነ አልሄድም። ምነው አጠገቤ በርበሬ የሚሸጥበት ሱቅ ቢኖር እላለሁ።

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement