በ2009 ዓ.ም ግንባታቸው ተጠናቆ ሥራ የጀመሩት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ተመን ወጥቶላቸው አገልግሎት እየሰጡ ነው ተባለ – Modern Public Car Park

                              

ምህረት ስዩም

በመገናኛ ዘፍመሽ የተገነባው የመኪና ማቆሚያ ቦታ በሰዓት 6 ብር በማስከፈል አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የመኪና ማቆሚያው በአካባቢው የተገነባው የሚታየውን የተጨናነቀ የመኪና ፍሰት ለማስቀረት በመሆኑ በአካባቢው መንገዶች ዳር ላይ መኪና ማቆም የተከለከለ ሲሆን ህጉን ባለማክበር መኪና የሚያቆሙ ግለሰቦች እየተቀጡ እንደሆነ ከአዲስ አበባ የትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ሰምተናል፡፡

ፓርኪንጉን በቋሚነት ለሚጠቀሙ ደንበኞችም በወርሃዊ የክፍያ ስርዓት እንዲስተናገዱ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የፓርኪንግ ቦታውን የሚያስተዳድረው የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ሲሆን በቀን እስከ አራት ሺ ብር የሚደርስ ገቢ ከመኪና ማቆሚያ ስፍራው እየተገኘ ነው ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል በወሎ ሰፈር የተገነባው የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ግንባታው አልቆ ሥራ ቢጀምርም ወደ መኪና ማቆሚያው የሚያስገባው መንገድ በግንባታ ላይ በመሆኑ የሚጠበቀውን ያህል ተጠቃሚ አላገኘም ተብሏል፡፡

ይህንንም ለማስተካከል መንገዱን ምቹ ማድረግና በአካባቢው ባልተፈቀደ ቦታ ተሽከርካሪያቸውን የሚያቆሙ ግለሰቦች ላይ ቁጥጥር ይደረጋል መባሉን ከፅህፈት ቤቱ ሰምተናል፡፡

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

 

Advertisement