አማዞንና ኢቤይ በቀጥታ ኢንተርኔት የሚፈፀምን የታክስ ማጭበርበር መቆጣጠር አለመቻላቸው ተነገረ

                                                           

አማዞንና ኢቤይን ጨምሮ ሌሎችም የቀጥታ ኢንተርኔት ግብይት ማስፈፀሚያ ኩባንያዎች በቀጥታ ኢንተርኔት የሚፈፀምን የታክስ ማጭበርበር መቆጣጠር እንዳልቻሉ የብሪታኒያ የህግ አውጭ ምክር ቤት አባላት ገለፁ።

ህግ አውጭ አባላቱ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከሀገሪቱ መንግስት የታክስ አስተዳደር ጋር እንዲሰሩ ነው ያሳሰቡት።

የኦዲት አስተዳደር እና ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት የታክስ አስተዳደር ተቋሙ እያንዳንዱ የቀጥታ ኢንተርኔት ግብይት ሻጭ እና ገዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፍል በማድረግ ረገድ ዝቅተኛ ውጤት ነው ያለው ብለዋል።

ታክሱን ያልከፈሉ ተቋማት ላይ ቁጥጥር ያለማድረግ ክፍተት መኖሩንም ጠቁመዋል።

በዚህ ከፍተት መንግስት ማግኘት የነበረበትን 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በየዓመቱ እያጣ መሆኑንም ገልጸዋል።

የቀጥታ ኢንተርኔት የግብይት ማዕከላት የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚያጭበረብሩ ሻጭ እና ሸማቾችን እንደሚቆጣጠሩ ቢናገሩም በተግባር ግን አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ ሆኖ መገኘቱን የኮሚቴው ሊቀመንበር ሜግ ሂሊየር ተናግረዋል።

በቀጥታ ኢንተርኔት የሚፈፀም የታክሰ ማጭበርበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሆኑም ተመላክቷል።

ለዚህም ምክንያቱ በኢንተርኔት ግብይት እንዲከናወን የሚያደርጉት ኩባንያዎች ሻጮች ከሚሸጡት ምርት መክፈል የሚጠበቅባቸውን 20 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳልከፈሉ በምትኩም ሁለቱን ብቻ ተጠቃሚ ማድረጋቸው ነው።

አማዞን እና ኢቤይ በበኩላቸው በቀጥታ ኢንተርኔት የሚፈፀም የተጨማሪ እሴት ታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ከታክሰ አስተዳደር መስሪያ ቤቱ ጋር እየሰራን ነው ብለዋል።

አማዞን በግሉ የታክሰ ህጎችን አክብረው ሽያጭ እና ግዥ የሚያከናውኑ ድርጅቶችን ከዝርዝሩ እንዲያስወጣ እና ግብይት እንዳያከናውኑ እንደሚከለክል ገልጿል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement