ለልጆች ደህንነት የተመረቱ ሰዓቶች በመረጃ ጠላፊዎች የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው

                                                      

ለህፃናት ደህንነት ተብለው የተዘጋጁ ስማርት ሰዓቶች ለመረጃ ጠላፊዎች ተጋላጭ የሚያደርጓቸው የደህንነት ጉድለቶች መኖራቸውን አንድ የክትትል ቡድን አስታወቀ።

ስማርት ሰዓቶች በአብዛኛው እንደ መሰረታዊ የስማርት ሞባይል ስልኮች አገልግሎት ያላቸው ሲሆን፥ ይህም ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እንዲነጋገሩ እና ልጆቻቸው እንዲከታተሉ የሚያስችል ነው ተብሏል።

የኖርዌይ ኮንሲዩመር ካውንስል (ኤን. ሲ. ሲ.) ጋቶር እና ጂ.ፒ.ኤስ. ለህጻናት ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ኩባንያዎች የሚያቀርቡዋቸው ስማርት ሰዓቶችን ፈትሾዋል።

የፍተሻው ውጤት እንደሚያመለክተውም አሁን በገበያ ላይ ያሉት የህፃናት ስማርት ሰዓቶች ጥቃት የሚሰነዝሩ ሰዎች ሊከታተሏቸው፣ ሊያደምጧቸው ወይም ከልብሶቻቸው ጋር በመገናኘት ለጠለፋ ምቹ ሊሆኑ ይችላሉ።

ይህን ተከትለው አምራቾችም ችግሮቹን እና መፍትሔዎችን በመፈለግ ላይ ናቸው ተብሏል።

ዋጋቸውም 131 የአሜሪካን ዶላር መሆኑን ተጠቁሟል።

የኖርዌይ ሸማች ካውንስል እንዳለው ጋቶር እና ጂ.ፒ.ኤስ. የተባሉ ለህፃናት የሚዘጋጁ ሰዓቶች ላይ ሙከራ አድርጓል።

ባደረገው ሙከራም በእነዚህ ሰዓቶች አማካይነት የመረጃ ጠላፊዎች ክትትል ሊያደርግ እና ሰዓቶቹን ከለበሱቸው ልጆእች ጋር የመልዕክት ለውውጥ በማድረግ አደጋ ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ደርሸበታለሁ ነው ያለው።

ይህ ማለት መሰረታዊ የጠለፋ ዘዴዎችን በመጠቀም ልጆች በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መከታተል ወይም ልጆች በተለየ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንዲገኝ ሊያደርግ ይችላሉ።

ሰዓቶችን የሚያመርተው ድርጅትም ተጨማሪ ምክር እና ማረጋገጫ ከአቅራቢው እስኪሰጠው ድረስ፥ አሁን ያለውን ስጋት እንደ ቅድመ ጥንቃቄ ወስዶ ምርቱን ለደንበኞች በመሸጥ ላይ እንደሆነ ተናግሯል።

የጋቶር ሰዓት አከፋፋይ ስጋቱን ለመቅረፍ የደህንነት ስልት ነድፎ እየሰራ መሆኑን ጠቅሶ፥ ለደንበኛ አዲስ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መተግበሪያ እያዘጋጀሁ ነው ብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement