ለመወገድ ከተዘጋጁ ዛፎች አስደናቂ ቅርጻ ቅርጾችን የሚሰራው ሮማኒያዊ

                                                                

ሮማኒያዊው የ42 አመት ጎልማሳ ጋቢ ሪዚያ በዛፎች ላይ በሚሰራቸው አስደናቂ ቅርጻ ቅርጾች ተቀባይነትን እያገኘ መጥቷል።

የቀድሞው የደን ተንከባካቢ ባለሙያ ጎልማሳ በሚኖርበት የክራዮቫ ከተማ መናፈሻ ፓርክ፥ በዛፎች ላይ አይን የሚስቡና ማራኪ ቅርጻ ቀርጾችን እየሰራ ነው።

ለዚህ ስራው ደግሞ እድሜ ጠገብውና በጡረታ ምክንያት ለመወገድ የተዘጋጁ ዛፎችን ብቻ ነው የሚጠቀመው።

ከቀድሞ ስራው ከተገለለ በኋላ ይህን የቅርጻ ቅርጽ ስራ የጀመረው ጎልማሳ፥ የሚሰራቸው ቅርጻ ቅርጾች በከተማዋ የሚገኘውን የመናፈሻ ፓርክ ውበት አላብሰውለታል።

የእርሱ ስራ በእድሜ መግፋት ምክንያት ይወገዱ የተባሉ ዛፎችንም ሙሉ በሙሉ ከመወገድ ታድጓቸዋል።

ተቆርጠው ሊወገዱ የተዘጋጁ ዛፎችን የተለየና ማራኪ ቅርጽ በመስጠት ባሉበት ቦታ የአካባቢው መስህብ እንዲሆኑም አድርጓቸዋል።

መጋዝ፣ መሮ እና መቁረጫ ግራይንደር በመጠቀም ከሰራቸው ቅርጻ ቅርጾች መካከልም፥ “ከባሊ በሚቀዳ ውሃ” ምስል የሰራው ቅርጽ ታዋቂነትን አትርፎለታል።

ይህን ስራውን ያዩ ሌሎች የሮማኒያ ከተማ አስተዳደሮችም ቀራጺውን በከተማቸው ተመሳሳዩን ይሰራ ዘንድ ጥሪ አቅርበውለታል።

የጋቢን የዛፍ ላይ አስደናቂ ቅርጻ ቅርጾች ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል፤

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement