“እንቁጣጣሽ” በሚለው ሙዚቃዋ የምትታወቀው ድምፃዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

                                                               

“እንቁጣጣሽ”፣ “ትዝታ በፖስታ”፣ “የጥበብ አበባ” እና በሌሎችም ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው ድምፃዊት ዘሪቱ ጌታሁን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ዘሪቱ ባደረባት ህመም ለረዥም ጊዜ በህክምና ስትረዳ ብትቆይም ዛሬ ረፋድ ላይ ህይወቷ አልፏል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትም ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጆቿ እና አድናቂዎቿ መፅናናትን ይመኛል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement