NEWS: የቻይና ተመራማሪዎች የሰዎችን ማንነት በአረማመዳቸው የሚለይ መሳሪያ ሰሩ

                                                       

የቻይና ተመራማሪዎች የሰዎችን ማንነት በአረማመዳቸው የሚለይ መሳሪያ ሰሩ።

ቴክኖሎጂው በተገጠመለት ካሜራም የሰዎችን ማንነት ለመለየት ፊታቸውን እይታ ውስጥ ሳያስገባ እስከ 50 ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ አረማመዳቸው አማካኝነት በፍጥነት ይለያል።

በቻይና የሳይንስ አካዳሚ የአውቶሜሽን ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች መሳሪያው ማንነትን ለመለየት ያሉትን ነባራዊ ሁኔታዎች መተንተን ያስፈልገዋል ነው ያሉት።

ይህ ቴክኖሎጂ በርካታ ጥቅሞችን ይዞ መምጣቱንም ገልፀዋል።

በቻይና የሳይንስ አካዳሚ ተባባሪ ተመራማሪ የሆኑት ሁዋንግ ዮንግዠን፥ ከዚህ ቀደም የነበሩት ቴክኖሎጂዎች ሰዎችን ለመለየት በአጭር ርቀት እና ረዥም ጊዜ ይወስዱ ነበር ብለዋል።

አሁን የተሰራው መሳሪያ ግን በብዙ ርቀት ላይ ያለን ሰው ማንነት በፍጥነት ለይቶ በአረማመዱ ማሳወቅ መቻሉ የራሱ ፋይዳ አለው ነው ያሉት።

ሰዎችን ለመለየት የሚወስድበት ጊዜ ከ200 ሚሊ ሰከንዶች ያነሰ ነው።

ቴክኖሎጂው ብዙ የህዝብ ቁጥርን አጠጋግቶ ለማወቅ የሚረዳ ሲሆን፥ በ1 ሺህ ስኩየር ሜትር ውስጥ ያሉ 1 ሺህ ሰዎችን መለየት ይችላል።

ይህ መሳሪያ ለደህንነት እና ለህዝብ ትራንስፖርት ስራዎች በዋናነት እንደሚያገለግል ተመራማሪዎች ጠቁመዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement