NEWS: በትግራይ ማዕከላዊ ዞን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲሳተፉ የነበሩ 21 ደላሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

                                                    

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲሳተፉ የነበሩ 21 ደላሎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ላይ ተሰማርተው ቆይቷዋል የተባሉት ደላሎች በቁጥጥር ስር የዋሉት ፖሊስና ህዝቡ በቅንጅት ባደረጉት የክትትል ሥራ ነው።

የወንጀል ምርመራ ዘርፍ አስተባባሪ ኮማንደር ጸሐዬ አረፋይኔ እንዳሉት፥ አራት ሴቶችን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ህገ ወጥ ደላሎቹ በአሁኑ ወቅት በ12 የክስ መዛግብት ተከሰው ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ይገኛል።

ፖሊስ ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ባለው አደረጃጀትና በሕብረሰተቡ የነቃ ተሳትፎ ደላሎቹ መያዛቸውን ጠቁመዋል።

በዞኑ “አሕፈሮም፣ መረብ ለኸ፣ ወርዒ ለኸና ዓብይ ዓዲ” ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በብዛት የሚፈጸምባቸው ወረዳዎች ናቸው።

ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በተሰራው ሥራም በአሁኑ ወቅት በወረዳዎቹ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር የመቀነስ አዝማማያ እያሳየ መምጣቱን ጠቁመዋል።

ሕብረተሰቡ በህገ ወጥ ስደት ላይ ያለውን ግንዛቤና አመለካከት ማደጉን ተከትሎ ደላሎችን ለመጠቆም ሆነ ዝውውሩን ለመከላከል እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚመሰገን ነው ብለዋል።

መንግስት በየጊዜው በሚሰጠው ስልጠና ህገ ወጥ ስደት መፍትሔ እንደማይሆን ለወጣቶች እያስተማረ መሆኑን ገልጸው ወጣቶች በሀገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ እየተደረገ ያለውን ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement