የድንገተኛ ልብ ሕመምን ለመከላከል

                                                    

 በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
እንደ ስንዴ፣ሲሪያል፣ ፍራፍሬ፣አትክልት እና አጃን መመገብ ከኮሌስትሮል ወደ ሰውነታችን እንዳይወስድ ማድረግ አቅም አለው
 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
እንቅስቃሴን ማድረግ ለድንገተኛ የልብ ሕመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ እንቅስቃሴ ያድርጉ
ለሰውንት ተስማሚ የሆኑ የስብ ዓይነቶችን ምግቦች መመገብ
ይህም ማለት ከስጋ እና ጮማ ከበዛባቸው ምግቦች ይልቅ እንደ አሳ፣ኦቾሎኒ፣እና አቮካዶ የመሳሰሉትን መመገብ
 ሲጋራ ማጤስን ማቆም
ሲጋራን በመደበኛ ሁኔታ የሚያጨሱ ከሆነ እራስዎን ለድንገተኛ የልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ ይዳርጋል
 የሚወስዱትን የጨው መጠን መቀነስ
ጨውን መመገብ የሚያዘወትሩ ከሆነ የደም ግፊትዎን እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ስለዚህ የሚመገቡትን የጨው መጠን ይቆጣጠሩ፣
 ጭንቀትን መቀነስ
ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት ካለብዎ ራስዎን ለአደጋ እየጣሉ ስለሆነ ለመቀነስ ይሞክሩ
 የስኳር መጠንዎን መቆጣጠር
የስኳር ሕመም ለልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጋልጥ ስለሆነ በሚገባ ይቆጣጠሩ
 የደም ግፊት መጠንዎን በሚገባ መቆጣጠር
የደም ግፊት ለልብ ሕመም ተጋላጭነትን ስለሚጨምር በሚገባ መቆጣጠር ይኖርብዎታል፡፡ መድኃኒት የሚወስዱም ከሆነ በሐኪምዎ ትዕዛዝ መሠረት ይተግበሩ
 የአልኮል መጠጥ ማስወገድ
አልኮልን በአብዛኛው የሚጠጡ ከሆነ እራስዎን ለደም ግፊት መጨመር ያጋልጣሉ ይህም በተዘዋዋሪ ለልብ ሕመም ይዳርግዎታል::

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement