በተመሳሳይ ሆስፒታል በአንድ ቀን የተወለዱት ጥንዶች ተጋብተዋል

                                                      

በአሜሪካ በማሳቹሴትስ ሆስፒታል በተመሳሳይ ቀን የተወለዱት ጥንዶች ጋብቻ ፈፅመዋል።

ከ20 ዓመታት በፊት ህክምና ማዕከል ሲወለዱ የተገናኙት ጥንዶች ግንኙነታቸውን ወደ ትዳር ቀይረዋል።

ጀሲካ ጎሜዝ እና አሮን ባሪዮስ በፈረንጆች ሚያዚያ 28 ቀን 1990 ነው የተወለዱት።

ከተወለዱ በኋላ በተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኙ መንደሮቻቸው ተነጣጥለው አድገዋል።

በትምህርታቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሲሆኑ፥ በአንድ ሆስፒታል በተመሳሳይ ቀን የተወለዱት ጀሲካ እና ባይሮስ ተመልሰው ተገናኙ፤ በሂደትም ጓደኝነት መሰረቱ።

ሁለቱ ጓደኛሞች በተመሳሳይ ቀን መወለዳቸውን ያወቁት በመንጃ ፈቃድ ትምህርት ቤት ውስጥ የተለማማጅነት መታወቂያ ሲያወጡ ነበር።

ጀሲካ እሷ ቀድማ ባይሮስን እንደወደደችው እና እንደ ጠየቀችው ተናግራለች።

አሁን ላይ በተመሳሳይ ቀን በተመሳሳይ ሆስፒታል የተወለዱት ጥንዶች ትዳር መስርተው ህይወትን በጋራ ጀምረዋል ተብሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement