ሁሉም ኳሶች ወንዝ ውስጥ በመግባታቸው የተቋረጠው የእግር ኳስ ጨዋ

                                                                                         

በሮማኒያ ሲካሄድ የነበረ አንድ ጨዋታ ሁሉም ኳሶች ወንዝ ውስጥ ውስጥ በመግባታቸው ተቋርጧል።

የእግር ኳስ ጨዋታዎች በአየር ሁኔታ ምቹ አለመሆን፣ ግጭት ሲፈጠር ወይም ግጥሚያ ለማድረግ የማያመቹ ሁኔታዎች ሲፈከሰቱ ሊቋጡ ይችላሉ።

በሮማኒያ ለተፈጠረው የእግር ኳስ ጨዋታ የቀረበው ምክንያት ግን ብዙዎችን አነጋግሯል።

በምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር የሚገኙት ቢስትሪታ ቢስቲሪታ ብሮስቴኒ እና ቫናቶሩል ዶርና ቻንድሬኒለር እግርኳስ ቡድኖች ጨዋታ ለማድረግ ቀነ ቀጠሮው ላይ ደርሰዋል።

የግጥሚያው እለት ደረሰ፥ ሁለቱም ክለቦች ጨዋታ ጀመሩ።

በዚህ ጊዜ ኳስ ወደ ውጭ ሲወጣ መጥፋት ጀመረ፤ ምክንያቱ ሲጠየቅ ደግሞ በስታዲየሙ አቅራቢያ ወንዝ በመኖሩ ኳሱ ወንዝ ውስጥ እየገባ ስለነበረ ነው።

ጨዋታው 58ኛው ደቂቃ ላይ ሲደርስ ባለሜዳዎቹ ብስቲርታ 2 ለ 0 እየመሩ 58 ደቂቃ ላይ እንደደረሱ ድንገት ሜዳው ኳስ አልባ ሆነ።

ሁሉም የእግር ኳሶች በስታዲየሙ አቅራቢያ በነበረው የብሪስቲታ ወንዝ በመግባታቸው ምክንያት ግጥሚያው ተቋረጠ።

በስታዲየሙ ውስጥ የሚገኙ ደጋፊዎችም ባልተለመደ ክስተት የጨዋታውን መቋረጥ ተከትሎ፥ “ኳሶቹን ከቢካዝ ግድብ አውጥታችሁ አምጡ” እያሉ መዘመር እና መጮህ ጀመሩ።

ቢካዝ በጨዋታው ሜዳ አቅራቢያ የሚገኝ ግድብ ነው።

ከዚህ ቀደም የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ባልተለመዱ ክስተቶች ተቋርጠው ያውቃሉ።

ባለፈው ዓመት ኤፍ ሲ ባሮሜትሪክስ ሻርፕነስን በገጠመበት ጨዋታ በ19 ደቂቃ ውስጥ ብቻ 5 ተጫዋቾቹ፥ ተገቢ ባልሆነ አጨዋወት ምክንያት ከሜዳ በመሰናበታቸው በስድስት ሰው ብቻ ለመጨረስ ተገዷል።

በእንግሊዝ በ977 ደርቢ ካውንቲ እና ማንቸስተር ሲቲ ሲያደርጉት የነበረ ጨዋታ፥ የፍፁም ቅጣት ምት የመምቻ ቦታ በመጥፋቱ ምክንያት ጨዋታው ተቋርጧል።

በ2015 ደግሞ ለ2016 የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ሰርቢያ እና አልባኒያ የሚያደርጉት ጨዋታ፥ ሰው አልባ አውሮፕላን በስታዲየሙ በማረፏ ምክንያት መቋረጡ ይታወሳል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement