NEWS: ተመራማሪዎች የኤች.አይ.ቪን ጉዳትና ተለዋዋጭነት 99 በመቶ የሚቀንስ መድሃኒት ሰሩ

                                                  

ተመራማሪዎች የኤች.አይ.ቪ ቫይረስን የጉዳት አቅም 99 በመቶ የሚገድል እና የመከላከል አቅምን የሚጨምር አዲስ ፀረ እንግዳ አካል መድሃኒት ( antibody) ሰሩ።

ፀረ እንግዳ አካል መድሃኒቱ የቫይረሱን ሶስት ወሳኝ የመስፋፊያ አካሎች በማጥቃት ነው የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደም ውስጥ የሚያደርሰውን ጉዳት የሚቀንሰው።

የአሜሪካ ብሄራዊ የጤና ኢንስቲትዩት እና ሳኖፊ የመድሃኒት ቅመማ ኩባንያ ናቸው አዲሱን የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒት ያገኙት።
ዓለም አቀፉ የኤድስ ማህበር ግኝቱን አስደናቂ ብሎታል።

የፀረ ኤች አይ ቪ መድሃኒቱ በፈረንጆቹ 2018 የመክላከል አቅሙና የቫይረሱን ጉዳት የመቀነስ ሃይሉ በሰዎች ላይ ይሞከራል ተብሏል።

ተመራማሪዎች “ቫይረሱ በደማችን ውስጥ ተፈጥሯዊ ቅርፁን እየቀያየረ ስለሚኖር ሰውነታችን በሽታውን ለመቋቋም ይፈተናል” ይላሉ።

አሁን የተሰራው የፀረ ኤች አይቪ መድሃኒት በ24 ዝንጀሮዎች ላይ ተሞክሮ የቫይረሱን ስርጭት 99 በመቶ ለይቶ እንደሚመታ እና እንደሚቀነሰው ተጠቁሟል።

በምርምሩ ላይ የቫርቫርድ የህክምና ትምህርት ቤት፣ የስችሪፕስ የምርምር ኢንስቲትዩት እና የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትም ተሳትፈዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement