NEWS: ሰሜን ኮሪያ በፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ የሀይድሮጅን ቦምብ እንደምትሞክር ዛተች

                                

የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፒዮንያንግን ላስፈራራው ንግግራቸው ምላሽ የሚሆን የሀይድሮጅን ቦምብ ሙከራ እንደሚያደርጉ ዛቱ።

መሪው የሀይድሮጅን ቦምቡን እሞክራለሁ ያሉት በፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ነው።

ትራምፕን “ድንጉጥ” ብለው የጠሩት ኪም ጆንግ ኡን በጉባኤው ላይ ላሰሙት ንግግር ዋጋ ይከፍላሉ ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለጉባኤው የመጀመሪያቸው በሆነው ንግግራቸው አገራቸው ራሷን እና አጋሮቿን ለመከላከል ከተገደደች ሰሜን ኮሪያን እንደምታወድም ተናግረው ነበር።

ይህን ተከትሎም ለጉባኤው ኒው ዮርክ የሚገኙት የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው በፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ድንገተኛ የሀይድሮግን ቦምብ ሙከራ እንደምታደርግ ተናግረዋል።

ኪም ጆንግ ኡን ለትራምፕ ንግግር በሚሰጠው ምላሽ ላይ እያሰቡ መሆናቸውን በመግለፅ፥ ምላሹም ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ያልተጠበቀ እንደሚሆን ነው የዛቱት።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement