የዛሬ የዕለተ አርብ መስከረም 12 ቀን 2010 የሸገር ወሬዎች

                                              

የመድኃኒት ፈንድ አቅርቦት ኤጀንሲ በ2009 ዓ.ም 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን መድኃኒቶች ለጤና ጣቢያዎች አከፋፈልኩ አለ፡፡ በዘንድሮውም አቅርቦት ጉዳይ ይመከርበታል ብሏል፡፡ (አስፋው ስለሺ)

በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሃገር ሊገባ የነበረ በርካታ መጠን ያለው ሺሻና የብር ጌጣ ጌጥ መያዙ ተሠማ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

በደጃች ውቤ በቀበሌ ቤቶች የሚኖሩ ሰዎች በሚጥለው ዝናብ ምክንያት ምንጩን ያላወቅነው ጎርፍ ቤት ውስጥ እየገባ ተቸግረናል እስከ ክፍለ ከተማ ሄደን ብናሳውቅም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡ (በየነ ወልዴ)

የአለም የቱሪዝም ቀን ሲከበር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን እንዲጎበኙ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተናግሯል፡፡ (ምሥክር አወል)

የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራች ድርጅቶች ተመርጦ ለገበያ የሚቀርበው መድኃኒት የአጠቃላይ ፍላጎቱ 15 በመቶ ብቻ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ለሥራዬ እንዲያመቸኝ ስድስት ዋና ዋና ቅርንጫፍ /ክላስተር/ መሥሪያ ቤቶችን ልከፍት ነው አለ፡፡ ንዑስ ቅርንጫፎቹን ደግሞ ከ17 ወደ 19 
ከፍ ሊያደርግ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ (አስፋው ስለሺ)

ተጠርጣሪዎች በምርመራ ወቅት ነፃ የህግ ድጋፍ የሚያገኙበት አሰራር በሀገራችን እየታሰበ ነው ተባለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በጋምቤላ አየር ማረፊያ ያስገነባው የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማ ተጠናቀቀ፡፡ (ማኅሌት ታደለ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement