ህንዳዊው ፕሮፌሰር ባለፉት 30 ዓመታት በተለያዩ የትምህርት መስኮች 145 ዲግሪዎችን አግኝተዋል

                                                          

ፕሮፌሰር ቪኤን ፓርቲባን በህንድ ቼናይ ነዋሪ ሲሆኑ፥ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

ፕሮፌሰር ፓርቲባን ባለፉት 30 ዓመታትም 145 ዲግሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች የያዙ ሲሆን፥ “በቀጣይም ትምህርት ማጥናቴን አላቆምም” ይላሉ።

የፕሮፌሰር ፓርቲባን ጉዞ የመጀሪያ ዲግሪያቸውን ሲመረቁ በተላዩ ችግሮች ውስጥ ሆነው ነበር።

ከተመረቁ በኋላም በህንድ የፍትህ መስሪያ ቤት ተቀጥረው መስራት ጀመሩ።

የተሰማሩበት ስራ ግን ትምህርት ከመማር አላገዳቸውም።

በአቅራቢያቸው በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ በተለየዩ የትምህርት መስኮች አንድ ሁለት እያሉ 145 ዲግሪዎችን መቀበል ችለዋል።

“ባለፉት 30 ዓመታት በስራ፣ በትምህርት፣ በፈተና እና በምርምር ውስጥ ነው ራሴን ያሳለፍኩት” ይላሉ።

አዳዲስ የዲግሪ እና የዲፕሎማ ትምህርቶች ሲመጡም እንደማያመልጣቸው ጠቁመዋል።

ፓርቲባን በሳይንስ ዘርፍ 3 የሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ፣ በህግ 8 የሁለተኛ ዲግሪ፣ በበንግድ ስራ ትምህርት 8 የሁለተኛ ዲግሪ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን 9 የሁለተኛ ዲግሪ፣ በአርትስ 10 የሁለተኛ ዲግሪ ፣ በተለያዩ የምርምር ትምህርቶች 12 ዲግሪ እና ሌሎችንም አሳክተዋል።

ፕሮፌሰሩ ሲማሩ ያልወደዱት የትምህርት መስክ አለ ወይ ተብለው ሲጠየቁ፥ በትክክል አዎ አለ እሱም “ሂሳብ” ነው ብለዋል።

እንዳልመታደል ሆኖ ፕሮፌሰር ፓርቲባን ያለፉትን 30 ዓመታት በትምህርት ለይ በማተኮራቸው አዕምሯቸው ከትምህርታዊ እውቀት ውጭ ቦታዎችን እና ሰዎችን ያለመለየት ችግር ፈጥሮባቸዋል።

የ56 ዓመቱ ህንዳዊ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያስተምሩ ሲሆን፥ ራሳቸውም እየተማሩ ነው።

ሚስት እና ሁለት ልጆች ያላቸው ፕሮፌሰሩ፥ ቤተሰባቸው ትምህርትን ዋነኛ የህይወት ግብ አድርግ በመጓዝ ይታወቃል ተብሏል።

የፕሮፌሰር ፓርቲባን ባለቤት 9 ዲግሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች የተቀበሉ ሲሆን፥ “ውድ ባለቤቴ ከእኔ ልትደርሽ 136 ስለሚቀርሽ ጠንክረሽ ተማሪ” ይሏቸዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement