ጃፓን ውስጥ እድሜያቸው ከ90 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን አልፏል ተባለ

                                                                     

ጃፓን ከዜጎቿ ውስጥ ከ2 ሚሊየን በላዩ እድሜያቸው ከ90 ዓመት በላይ መሆኑን የሀገሪቱ መንግስት በትናንትናው እለት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በጃፓን እድሜያቸው ከ90 ዓመት በላይ የሆኑ አዛውንቶች ቁጥር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር ከ2004 ወዲህ በእጥፍ ጨምሯል የተባለ ሲሆን፥ በወቅቱ የነበረው ቁጥርም 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብቻ ነበር።

ከዚህ በተጨማሪም ከሀገሪቱ ህዝቦች ውስጥ 35 ሚሊየኑ እድሜያቸው ከ65 በላይ ነው የተባለ ሲሆን፥ ይህም ሀገሪቱ ካላት አጠቃላይ የህብዝ ቁጥር 27 ነጥብ 7 በመቶውን የሚሸፍን ነው ተብሏል።

እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ ከሆኑት ውስጥ 7 ነጥብ 7 ሚሊየኑ ስራ እንዳላቸው የተገለፀ ሲሆን፥ የሀገሪቱን የሰራተኛ የሰው ሀይል ፍላጎትን በ11 ነጥብ 9 በመቶ እንደሚሸፍኑም ተገልጿል። 

“በጃፓን አድሜያቸው የገፉ ሰዎች በጣም ስራ መስራት ይፈልጋሉ፤ በርካታ ኩባንያዎቸም እየተቀበሏቸው ነው” ይላል በሚኒስትር ማእረግ የሀገሪቲ ስታስቲክስ ቢሮ።

የጃፓን አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር 127 ሚሊየን ሲሆን፥ ይህም አሜሪከ በአጠቃላይ ካላት 323 ሚሊየን ጋር ሰነጻጸር አንድ ሶስተኛውን ቢሸፍን ነው።

ሆኖም ግን እድሜያቸው ከ90 ዓመት ያለፉት ሰዎች ቁጥር ከአሜሪካ ጋር ሲነጻጸር የጃፓን አብላጫ እንዳለው ነው የሚነገረው።

አሜሪካ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2010 በተካሄደው ቆጠራ እድሜያቸው ከ90 ዓመት ያለፉ ሰዎች ቁጥር 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ሲሆን፥ የጃፓን ግን ከ2 ሚሊን አልፏል።

በጃፓን ያለው ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት የሀገሪቱ ዜጎች ረጅም እድሜን እንዲኖሩ እያገዘ ነው ቢባልም፤ የእድሜ መግፋት አሁንም ሀገሪቱ ላይ ችግር ማስከተሉን አላቆመም።

የጃፓን ፖሊስ ባላፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2015 ብቻ ከእድሜ ጋር ተያይዞ በሚከሰት የአእምሮ መሳት ችግር 12 ሺህ ሰዎች ከሚኖሪያቸው ጠፍተዋል።

ከእነዚሀም ወስጥ 479 አዛውንቶች ሞተው መገኘታቸውን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement