NEWS: ተመራማሪዎች የልጆችን ሁሉንም ክትባቶች በአንድ መርፌ መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ፈጠሩ

                                       

የአሜሪካ ተመራማሪዎች ሁሉንም የልጆች ክትባቶችን በአንድ መርፌ በመውጋት የሚሰጥ ቴክኖሎጂ ፈጠሩ።

ይህ ክትባቶችን ሁሉ በአንድ የመርፌ ህክምና ማድረስ የሚያስችለው መፍትሄ ክትባቱን በአነስተኛ መመጠኛ መሳሪያ በመለካት እንደሁኔታው መጨመር የሚያስችል ነው ተብሏል።

የምርምር ግኝቱ በዓይጦች ላይ ተሞክሮ ስኬታማ መሆኑ ተነግሯል።

ቴክኖሎጂው በዓለም የሚገኙ በርካታ ሰዎችን ከህመም ሊታደጋቸው የሚችል ነው ብለዋል ተመራማሪዎቹ።

ከዚህ በፊት የህፃናት የበሽታ መከላከያ ክትባቶች በሚዋጥ ወይም በሚቀባ መልኩ ነበር የሚዘጋጁት።

የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ለህጻናት የሚሰጡ ክትባቶችን በማዋሃድ በአንድ መርፌ መስጠት የምታስችል አነስተኛ ቴክኖሎጂ ፈጥረዋል።

መሳሪያዋ በጣም አነስተኛ የቡና መጠጫ ስኒ የምታክል ሲሆን በክትባት ከተሞላች በኋላ መከፈት በሚችል ቁስ ትገጠማለች።

የስኒዋ ቅርፅ መለዋወጥ የሚችል በመሆኑ ስኒዋን ሰብሮ የክትባቶችን ዓይነት በተፈለገው ጊዜ መገምገም ይቻላል ነው የተባለው።

በዓይጦች ላይ በተሰራው ሙከራ የክትባቶቹ ለውጥ በ9፣ በ20 እና በ41 ቀናት ልዩነት ታይቷል።

ሆኖም እስካሁን በሰዎች ላይ ሙከራ አልተደረገበትም ነው የተባለው።

በተለይም በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የክትባት ቴክኖሎጂው ፋይዳው የጎላ ሊሆን እንደሚችል ፕሮፌሰር ሮበርት ላንገር ተናግረዋል።

የክትባቱ ቴክኖሎጂዋ በሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓት ውስጥ ያለውን ፋይዳ በጉልህ በማሳወቅ ረገድ አስትዋፅኦዋ ቀላል አይደለም።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement