ሳይነሳይተስ – Sinusitis

                                 

ሳይነሳይተስ አፍንጫ አካባቢ የሰውነት ክፍል መቆጣት /inflammation/ ሲሆን ሁልጊዜ በባክቴሪያ፣ቫይረስና ፈንገስ ኢንፌክሽን አማካኝነት ይከሰታል::
ህመሙ በዓይን እና አፍንጫ አካባቢ ወይም የአፍንጫ ፈሳሽ ያስከትላል, አልፎ አልፎ የጥርስ ህመም፣ ትኩሳት ስሜት የመቅመስ እና የማሽተት ችግር ሊስከትል ይችላል::

ምልክቶች/symptoms/
-ራስ ምታት
-ከአፍንጫ ውስጥ ቢጫነት ያለው ፈሳሽ መታየትና አክታ ያለው ሳል
-ትኩሳት
-የመቅመስና የማሽተት አቅም መቀነስ

ጠቃሚ ምክሮች
-በየቀኑ በቂ ፈሳሽ መውሰድ
-በጀርባ መተኛት 
-ቅዝቃዜን መከላከል

አማራጭ የቤት ውስጥ ህክምና
1.ቀዝቃዛ ፎጣ በፊት ላይ ከ5-10 ደቂቃ ማስቀመጥ በቀን ውስጥ መደጋገም ህመሙን ቀንሳል::
2.በእንፋሎት መታጠን/STEAM INHALATION/
ከ3-4 ጠብታ የባህር ዛፍ ዘይት በውሀ በማፍላት መታጠን
3.የአፍንጫ ጠብታ/nasal drops/
ግማሽ ማንኪያ ጨው በግማሽ ብርጭቆ ውሀ ማዘጋጀት ነቀን ከ3-4 ጠብታ በአፍንጫ መጠቀም ደጋግሞ በቀን እስከ 6 ጊዜ መውሰድ ሙከሱን በመቀነስ ትንፋሽን ያስተካክላል::

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement