NEWS: ትራምፕ ኮንግረሱን በጎርፍ ለተጎዱት ግዛቶች የሚሆን 7 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር የመቋቋሚያ በጀት ጠየቁ

                                                        

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልደ ትራምፕ ቴክሳስ እና ሉዚያና ግዛቶች የጎርፍ አደጋው ካደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ የሚውል 7 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በጀት ኮንግረሱን ጠየቁ።

በሁለቱ ግዛቶች ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ያስከተለው ጉዳት መጠን ሙሉ በሙሉ ባለመታወቁም ተጨማሪ የገንዘብ ጥያቄ እንደሚኖር ነው የአገሪቱ መንግስት እያሳወቀ ያለው።

በአከባቢዎቹ በጎርፉ ምክንያት ቀያቸውን ለቀው ወጡ ነዋሪዎች አሁን ወደቤታቸው እንዲመለሱ ቢፈቀድም፥ አሁንም አከባቢውን ያጥለቀለቀው ውሃ መጠን አለመቀነሱ ተነግሯል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ ቴክሳስን የሚጎበኙ ይሆናል።

በዚህ የተፈጥሮ አደጋ 47 ሰዎች ሲሞቱ 43 ሺህ ሰዎች ደግሞ በመጠለያ ውስጥ ለመኖር ተገደዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement