NEWS: በመላ ሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ ለጎርፍ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ 12 አካባቢዎች ተለዩ

                                         

በተመስገን እንዳለ

 በመላው ሀገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ ለጎርፍ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ 12 አካባቢዎችን በጥናት መለየቱን የእረሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከዓለም የምግበ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ጋር በመተባበር ባካሄደው ጥናት፥ ድሬ ዳዋን ጨምሮ በአራት ክልሎች በከፍተኛ ደረጃ ለጎርፍ ተጋላጭ ናቸው የተባሉ ቦታዎችን መለየቱን ገልጿል።

በእረሻ እና ተፈጥሮ ሀበት ሚኒስትር የመሰረተ ልማት አማካሪ አቶ አክሊሉ መስፍን፥ በጥናቱ ለጉዳት ተጋላጭነታቸው በተጨማሪ የችግሩ ስፋት እና መፍትሄዎች ተለይተዋል ይላሉ።

ቦታዎቹ ለአደጋ ተገላጭ የሆኑበትን ምክንያት ውስጥም ቀዳሚው ትከክለኛ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም አለመኖሩ ነው ይላሉ አቶ አክሊሉ።

የመሬት መራቆት እና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች የጎርፍ አወጋገድ ላይ ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖሩ ለችግሩ በጥናቱ ላይ በምክንያትነት ተመላክቷል።

በዚህ ምክንያትም በርካታ ዜጎች ለሞት፣ ሀብት ንበረታቸው ደግሞ ለውድመት መዳረጉን ነው አቶ አክሊሉ የሚናገሩት።

የእረሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ዴታ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ በበኩላቸው፥ በጥናት በተለዩ 12 ቦታዎች የሚኖሩ ዜጎችን ለመታደግ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው በጊዜያዊነት እና በዘላቂነት አሰራር በመዘርጋት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩን በዋነኝነት መፍታት የሚቻለው ለአየር ንበረት ያለንን ተጋላጭነት በመቀነስ ነው ያሉት ዶክተር ካባ፥ በዚህ ዓመትም ከ19 ሚሊየን ህዝብ በላይ የተሳተፈበት የአካባቢ ጥበቃ እና የተፋሰስ ስራ ተከናውኗል ብለዋል።

የተለያዩ ክልሎችም በእንዲህ መልኩ ጉዳት እያደረሰ ያለውን የጎርፍ አደጋ ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

የደቡብ ክልል የእረሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ መለስ አማና፥ ክልሉ ከፌደራል መንግስት ጋር በመቀናጀት ለጎርፍ ተጋላጭ ቦታዎችን የመለየት ስራዎች ሲያከናውን መቆየቱን ይናገራሉ።

ክልሉ በ2009 በጀት ዓመት 20 ሚሊየን ብር መድቦ ዘላቂ የጎርፍ መከላከል ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ሲሉም አቶ መለሰ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ግበርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አይተነው እንደሻው በበኩላቸው፥ በክልሉ ለጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ተብለዉ የተለዩ አካባቢዎችን በዘላቂነት ከችገራቸው ለማስወጣት የተሰራው ስራ አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ።

የጎርፍ ተጋላጭነትን በዘላቂነት መፍታት የሚቻለው የአካባቢ ጥበቃ እና የተፋሰስ ስራዎችን በመስራት ነው የሚሉት ምክትል ሃላፊዉ፥ እስካሁን ከ7 ሚሊየን የሚበልጥ መሬት የተፈጥሮ ሀብተ ጥበቃ ተደርጎለት እንዲያገግም ተደርጓል።

እንደ ምክትል ሀላፊዉ ገለፃ በከፍተኛ ተደፋት አካባቢ የሚደርሱ የጎርፍ አደጋዎችን ለመከላከል የጎርፍ መከላከያ እና መቀልበሻ እየተሰሩ ነዉ።

የኦሮሚያ ክልል እረሻ እና ተፈጥሮ ሀብተ ቢሮ ምከትል ሃላፊ አቶ ደሳለኝ፥ እስካሀን ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ተብለው በተለዩ አካባቢዎች ህበረተሰቡን በማሳተፍ የተለያዩ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች መሰራታቸውንም አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል።

በዚህ ዓመትም ዓመት ብቻ ከ3 ቢሊየን በላይ ችግኝ በክልሉ መተከሉን የገለፁት ምክትል ሃላፊው፥ ለጎርፈ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀንሰ የጎርፍ መቀልበሻ እና መከላከያዎች እየተሰሩ ነዉ ብለዋል።

የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመላክተው በዚህ ዓመት ከ1 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ መሬት የአከባቢ ጥበቃ ስራዎች የተከናወኑለት ሲሆን፥ ከ146 ሚሊየን ቶን በላይ አፈር መጠበቅ ተችሏል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement