የዛሬ የዕለተ አርብ ነሐሴ 19 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች

                                   

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የወደፊት ታሳቢ የምርት አቅርቦትና ዝውውር ማከናወኛ መላ ሥራ ላይ ላውል ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ደንብን ለማስከበር የሚወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ምንም አይነት የህግ ማዕቀፍ የላቸውም አለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት ሠራተኞችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ደንብ እያዘጋጀ ነው፡፡ (በየነ ወልዴ)

የኢትዮጵያ የእንስሣት እርባታ ባለሙያዎች ማህበር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የበኩሌን ለመወጣት እድል ሊሰጠኝ ይገባል አለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)

ለጤና ጐጂ ንጥረ ነገር ይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ አምስት የምግብ አይነቶች ናሙናቸው ከገበያ ተወስዶ ጥናት እየተደረገባቸው ነው፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

ሰቆጣ ማይኒንግ የተባለውና በማዕድን ዘርፍ የተሰማራው ኩባንያ በኢትዮጵያ የብረት ማዕድን ለመሰማራት ግማሽ ቢሊየን ዶላር ማዘጋጀቱ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ የወጪ ንግድ መዳከም አንዱ ምክንያት አለም አቀፍ መስፈርትን አሟልተው አለመገኘታቸው ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

ከአዲስ አበባ ታክሲ አሽከርካሪዎች ስለ ትራፊክ አደጋ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ አሰጣጥ እውቀቱ ያላቸው ከ13 በመቶ አይበልጡም ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ካሣ ከፈልኩ አለ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

ኢትዮጵያ የአቮካዶ ምርት ለአውሮፓ ገበያ ማቅረብ ጀመረች ተባለ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement