NEWS: የሌሴቶው ንጉስ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው::

                                           

የሌሴቶው ንጉስ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተነግሯል።

የሌሴቶው ንጉስ ሌቲሴ 3ኛ ከመጭው ሰኞ ነሃሴ 15 2009 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት ለአራት ቀናት የሚቆይ መሆኑን ተገልጿል።

በቆይታቸውም በምስራቅ አፍሪካ እና በኢትዮጵያ የምግብና ግብርና ድርጅት (ፋኦ) ተወካዮች በኩል በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ገለጻ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡

ንጉስ ሌቲሴ 3ኛ ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩም ይጠበቃል።

ንጉስ ሌቲሴ 3ኛ በቆይታቸው ደቡብ ብሄር በሄረሰቦችና ህዝቦች ክልልን እንዲሁም ቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክንና የአየር መንገድ አቭዬሽን አካዳሚን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement