NEWS: በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በደረሰ የመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎችና የአራት ፍየሎች ህይወት ጠፋ

                                             

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጃርሶ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች የደረስ የመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎችና የአራት ፍየሎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

በሙለታና መልካ ጀብዱ ቀበሌዎች ነሐሴ 7 2009 ዓ.ም ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል እስከ አምሰት ሰዓት ተኩል የጣለውን ከባድ ዝናብ የመብረቅ አደጋ ተከስቷል፡፡

በዚህም የሙለታ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የ47 ዓመቱ አቶ አብራሂም አልዪ እና የ33 ዓመቷ የመልካ ጀብዱ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ አሚና አብዶ ወዲያውኑ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ፡፡

አቶ አብራሂም ሕይወታቸው ያለፈው በጉዞ ላይ እያሉ የጣለውን ከባድ ዝናብ ለማምለጥ ከትልቅ ዛፍ ስር ተጠልለው በነበሩበት ወቅት በወደቀ መብረቅ ነው፡፡

የወይዘሮ አሚናን ህይወት የቀጠፈው መብረቅ የወይዘሮዋን አራት ፍየሎች ህይወት ሲያጠፋ ቤታቸውንም አቃጥሏል፡፡

በቤት ውስጥ የነበሩ የወይዘሮ አሚና አራት ህጻናት ልጆቻቸው በመብረቁ ሳቢያ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ቢሆንም በአካባቢው ማህበረሰብ ርብርብ ህይወታቸው ተርፏል፡፡

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement