የዛሬ የዕለተ ሐሙስ ነሐሴ 11 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች::

                                    

በህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ደላሎች ላይ የሚደረገው ዘመቻ ቀጥሏል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

ቀደም ሲል ታውጀው ያተዘጉ እና በከፊል ላልተረጋገጡ ይዞታዎች ወሰን ተካሏል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

ኢትዮጵያ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶቿን ልኬት ስታትስቲክስ የሚያሳይ ጥናታዊ መረጃ እንደሌላት ተነገረ፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ በረራውን ዛሬ ወደ ባህሬን ይጀምራል ተባለ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት ከዘጠኝ መቶ የሚበልጡ የኢትዮጵያ ደረጃዎችን አፀደቀ፡፡ (ንጋቱ ርጋሣ)

በአዲስ አበባ የተቋማትን የሥራ መጣጣም የሚከታተል መሥሪያ ቤት በመቋቋሙ ከእንግዲህ አንዱ ሲገነባ ሌላው የሚያፈርስበት አጋጣሚ አይኖርም ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)

የቻይናው ኤግዚም ባንክ ለሰሜን አዲስ አበባ የውሃ አቅርቦት ችግር ማቃለያ ለሚከናወን ሥራ የሚውል የ146 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጠ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

ሱዳን የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የተለያዩ ቦታዎችን መጐብኘታቸው ተነገረ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement