SPORT NEWS: በደቡብ ክልል ሀዋሳ ከተማ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 5ኛው ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ፕሮጀክት የምዘና ውድድር ቀጥሎ እየተካሄደ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

                                       

በወንዶች እና በሴቶች የብስክሌት ውድድር የፍጻሜ ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን በወንዶች 10 ኪሎ ሜትር የግል ክሮኖ ሜትር የትግራይ ክልል  የወርቅ እና የነሐስ ሜዳሊያ ሲያገኝ ድሬዳዋ ክልል ደግሞ የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችሏል:: በሴቶች በተደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የግል ክሮኖ ሜትር የአማራ ክልል የወርቅ ፣ የትግራይ ክልል የብር እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል የነሐስ ሜዳልያ አግኝተዋል።

ትላንት  በተካሄደ የወንዶች የእግር ኳስ የምድብ ጨዋታ ኦሮሚያ ጋምቤላን 5 ለ 0 ፥ ሀረሪ ኢትዮ ሱማሌን 2 ለ 0 ፥ ትግራይ ድሬዳዋን 4 ለ 2 ሲያሸንፉ አፋር ከቤንሻጉል 1 ለ 1 በመሆን ጨዋታቸውን አጠናቀዋል ።

በወንዶች በቮሊ ቦል የምድብ ጨዋታ ኦሮሚያ አዲስ አበባን 3 ለ 0 ፥ ደቡብ ጋምቤላን በተመሳሳይ ውጤት 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል ። በሴቶች እጅ ኳስ ሴቶች ኦሮሚያ ከሀረሪ 10 ለ 8 ፥ ደቡብ ከትግራይ 31 ለ 13 ሲያሸንፉ ፡ በወንዶች ኦሮሚያ ከሀረሪ 25 ለ 13 ፥ አዲስ አበባ ከትግራይ 25 ለ 23 በሆነ ውጤት ተጠናቋል ።

በወንዶች ቅርጫት ኳስ ኦሮሚያ ከ አማራ 45 ለ 43 እንዲሁም በሴቶች ኦሮሚያ ከትግራይ 22 ለ 18 አሸንፈዋል። ውድድሩ ለቀጣይ ቀናቶችም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ብቁ የሆኑ ተወዳዳሪችም ምዘናውን አልፈው ወደ አካዳሚዎች የሚገቡ ይሆናል፡፡

ምንጭ:- ኢትዮአዲስ ስፖርት

Advertisement