የዛሬ የዕለተ ረቡዕ ነሐሴ 10 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች

                                               

በመጪዎቹ ስድስት ቀናት በክረምቱ ዝናብ የሚያገኙ አካባቢዎች ላይ ጠንከር ያለ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ጥንቃቄ አድርጉ ሲል የብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡ (ምህረት ስዩም)

ለደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የተሰጠው ተጨማሪ 10 ቀናት ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ እስከ ዛሬ ያልከፈሉ ከነገ ጀምሮ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

በካርቱም በሥራ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ለሁለተኛ ቀን ከካርቱም መሪዎች ጋር እየመከሩ ይገኛሉ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

ከ5 ዓመት በታች በሆኑ ኢትዮጵያውያን ህፃናት ላይ የደም ማነስ ችግር መጨመር ታይቷል ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)

በሐምሌ ወር ከእንስሣት ክትባት ሽያጭ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኘ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

የጀርመን መንግሥት ከሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ለተነሱ ሰዎች ድጋፍ አደርጋለሁ አለ ተባለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

በኢትዮጵያ የኩላሊት ንቅለ ተከላ የሚመራና የሚተዳደርበትን ሕግ የማርቀቅ ኃሣብ እንዳለ ተሠማ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

ኤርፖርቶች ድርጅቶች 5 አዳዲስ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ለመገንባት ቦታ መረጣ ላይ ነኝ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

ለሀጅ ጉዞ ወደ ሳዑዲ የሚሄደው የልዑካን ቡድን ውጡልን የተባሉና በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማግባባት ጥረት ያደርጋል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

በኦሮሚያ ክልል የወንዝ ሙላትና ጐርፍ ያሰጋቸው ወደ 1 ሺ የሚጠጉ አባወራዎች ወደ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲገቡ ተደረገ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

ዓለም አቀፉ ድርጅት ለአንኮበር ወረዳ አልዩ አምባ ዙሪያ ቀበሌ ልማት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

Advertisement