የዛሬ የዕለተ ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች

                                       

በሃያት ቁጥር 2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች በአካባቢው ዘራፊዎች አማረውናል እያሉ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ችግሩ ስለመኖሩ አምኖ መላ ለመፈለግ አዲስ መርሃ-ግብር ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)

በአዳማ ከተማም ቀማኞች አስቸግረዋል ተብሏል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

በኢትዮጵያ ለልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ጥቂት ሃኪሞች ቢኖሩም በህክምና ቦታ መስጫ እጦት ምክንያት እንደልብ እየሰሩ አይደለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

በትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ ከዚህ ቀደም ያጋጠመውን አይነት ውድቀት ላለመድገም ፕሮጀክቶች የሚጀመሩት በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲፀድቁ ብቻ ነው ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

የራስ አበበ አረጋይ ቤትና የተፈጥሮ ሐበት ቤተ-መዘክር በቅርስነት ቢመዘገቡም አፍርሱ ተብለናል ባሉ ተቋራጮች እየፈረሱ ነው ተባለ፡፡ (ምሥክር አወል)

ከየመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሽያጭ የሚወገዱ አሮጌ ጐማዎች የአካባቢ ብክለት የማያደርሱበት መላ እየተጠና መሆኑ ተሠማ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

የኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅራቢው መሥሪያ ቤት ድቤ ወስደው ያልከፈሉኝን ፋብሪካዎች ችሎት ልገትራቸው ነው አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

ከግል ድርጅቶች ሠራተኞች ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የጡረታ መዋጮ ባለፈው አመት መሰብሰቡ ተሰማ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

ኢትዮጵያ ለጐረቤት ሀገር ልካ ከሸጠችው ኤሌክትሪክ ኃይል ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተሰማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

መሠረት በጐ አድራጐት ድርጅት ለ15 ሺ ህፃናት የትምህርት ቁሣቁስ እያሰባሰብኩ ነው አለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement