NEWS: ወደ የመን ለመሻገር ሲሞክሩ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን መካከል 50 ያህሉ በህገ ወስጥ አዘዋዋሪዎች ሆን ተብለው ወደ ባህር ተጥለዋል፡፡

                                  

የዓለም የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM) ትላንት እንዳስታወቀው ወደ የመን ለመሻገር ሲሞክሩ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን መካከል 50 ያህሉ በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ሆን

ተብለው ወደ ባህር ተጥለዋል፡፡ የተረፉት 29ኙን በባህር ዳርቻ ቀብረዋቸው ማግኘቱን ሃያ ሁለት ስደተኞች ግን ደብዛቸው መጥፋቱን ገልጿል፡፡ ስደተኞቹ አማካይ ዕድሜያቸው 16

እንደሆነ ጠቅሷል፡፡ እንደ ድርጅቱ ዘገባ ካለፈው ጥር ጀምሮ 55 ሺህ የአፍሪቃ ቀንድ ስደተኞች የመን ተሰድደዋል፡፡ የትላንቱ አደጋ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ይልቅ በጦርነት እየታመሰች

ወደምትገኘው የመን መጓዝ የመረጡበትን መሰረታዊ ችግር ምንድነው? የሚለውኝ ጥያቄ እንደገና ቀስቅሷል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ ስደተኞችን ለማስወጣት ቀነ ገደብ በሰጠችበት በዚህ ወቅት

የስደተኞች ፍልሰት አለመገታቱም አጠያይቋል፡፡ እርስዎ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አልዎት? አስተያየትዎን በድምጽም ሆነ በጽሁፍ በዋትስ አፕ ለማካፈል ከፈለጋችሁ ወቅታዊ

ቁጥራችንን ይህንን አድራሻ ስትጫኑ ታገኛላችሁ። መመሪያውን ተከተሉ።

ምንጭ:-DW 

 

Advertisement