SPORT: ቅዱስ ጊዮርጊስ ታደለ መንገሻን በሁለት አመት ኮንትራት አስፈረመ::

                                          

ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀድሞ ተጫዋቹ ታደለ መንገሻን በድጋሚ አስፈርሞታል።

የቀድሞ የፈረሰኞቹ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ከክለቡ ጋር እስከ 2011 ዓ.ም ለሁለት አመት የሚያቆየውን ፊርማ አኑሯል።

ፈረሰኞቹ ከታደለ ዝውውር ባለፈ የክለቡ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው የናትናኤል ዘለቀን ውልም አራዝመዋል።

ናትናኤል ሰኔ 30 የተጠናቀቀውን ውሉን ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ነው ያራዘመው።

የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚህ ቀደም የደጉ ደበበ፣ በሃይሉ አሰፋንና ምንተስኖት አዳነን ኮንትራት ማራዘሙ የሚታወስ ነው።

በሌሎች የሃገር ውስጥ የዝውውር ዜናዎች ደግሞ ዘንድሮ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደጉት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና መቐለ ከተማ ክለባቸውን እያጠናከሩ ነው።

ወልዋሎ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም፥ የኢትዮ ኤሌክትሪኩን አማካይ ዋለልኝ ገብሬን፣ ቢንያም አየለን ከአዳማ ከተማ እና ተስፋዬ ዲባባን ከድሬዳዋ ከተማ አስፈርሟል።

የባህር ዳር ከተማውን ግብ ጠባቂ ዘውዱ መስፍን እንዲሁም እዮብ ወልደማርያምን ደግሞ ከአማራ ውሀ ስራ ማስፈረም ችሏል።

ከዚህ ባለፈም በውድድር አመቱ አጋማሽ ከድሬዳዋ ከተማ በውሰት ያመጡትን አሳሪ አልመሀዲን በቋሚነት አስፈርመዋል፡፡ 

ወልዋሎ ከቀናት በፊት የግራ መስመር ተከላካዩ ሮቤል ግርማን በሁለት አመት ኮንትራት ሲያስፈርም፥ የበረከት አማረ፣ ሳምሶን ተካ እና ኤፍሬም ጌታቸውን ውልም አድሷል።

ሌላኛው የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ክለብ የሆነው መቐለ ከተማ ጫላ ድሪባ እና ታደለ ባይሳን የግሉ አድርጓል፡፡

ጫላ ድሪባን ከወልዲያ እንዲሁም የመሃል ተከላካዩ ታደለ ባይሳን ከፋሲል ከነማ የግሉ ማድረግ ችሏል።

 

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

 

Advertisement