NEWS: ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 10’ን በአይናችን እንቅስቃሴ እንድናዝ ሊያደርግ ነው

                                    

ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ 10 ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ላይ አዲስ ነገር ለመጨመር እየሰራ መሆኑ ተሰምቷል።

ኩባንያው እየሰራው ያለው አዲሱ ቴክኖሊጂ ዊንዶውስ 10 በአይን ለመቆጣጣር የሚያስችል ሲሆን፥ በተለይም በጤና እከል ምክንያት ሰወንታቸውን ማንቀሳቀስ ለማይችሉት ይህ መልካም ዜና ነው ተብሏል።

አዲሱ ስሪት “በአይን መቆጣጣሪያ (Eye control)” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፥ ይህም ተጠቃሚዎች ያለ ምንም የእጅ ንክኪ አይናቸውን ብቻ በመጠቀም ዊንዶወስ 10 ኮምፒውተራቸውን እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነው።

የአይን መቆጣጣሪያውን የሚጠቀሙ ሰዎችም አይናቸውን ማንቀሳቀስ ብቻ ይጠበቅባቸዋል የተባለ ሲሆን፥ ይህም የአይን እንቅስቃሴን በሚከታተል ሀርድዌር መሳሪያ አማካኝነት የአይን እንቅስቃሴው ክትትል ይደረግበታል።

በዚህም ተጠቃሚዎች ከኮምፒውተራቸው ላይ የፈለጉትን መተግበሪያ መክፈት እና መዝጋት እንዲሁም ወደ ላይ እና ወደ ታች እያንቀሳቀሱ ኮምፒተራቸውን መጠቀም ይችላሉ።

ይህን ለማድረግም የሚፈልጉት ስፍራ ላይ በትኩረት ብቻ መመልከት በቂ ነው ተብሏል። 

ከዚህ በተጨማሪም በኮምፒውተሩ ስክሪን ላይ በሚመጣ መተየቢያ (ኪቦርድ) አማካኝነት ያለ ምንም የእጅ ንከኪ በአይን ብቻ እያዩ እንዲፅፉም ያደርጋል ተብሏል። 

አዲሱ የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 10 የአይን መቆጣጣሪያ ስሪት አሁን በሙከራ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን፥ በቅርቡም ተጠቃሚዎች ዘንድ መድረስ እንደሚጀምርም ተነግሯል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement