ቸኮሌት መመገብ በጭንቅላት ውስጥ የደም መፍሰስ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ አንድ ጥናት አመላከተ::

ቸኮሌት ከጣፋጭነቱ ባሻገር ለጤና እንደሚበጅ ይነገራል፤ በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ ጥናቶችም ይህ ጣፋጭ ብዙ የጤና አበርክቶዎች እንዳሉት ያሳያሉ።

ከሰሞኑ ይፋ የሆነ ጥናት ደግሞ ቸኮሌትን መመገብ የጭንቅላት ደም መፍሰስ ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ያሳያል።

በዴንማርክ የተደረገው ጥናት ከ50 እስከ 64 አመት እድሜ የሚገኙ ከ55 ሺህ በላይ ሰዎችን አሳትፋል።

በጥናቱም ሰዎቹ በሳምንት ውስጥ የቸኮሌት ፍጆታቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ነው ጥናቱ የተደረገው።

ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች ቸኮሌት እንዲመገበቡ የተደረገ ሲሆን፥ የተወሰኑት ከፍላጎት አንጻር በተፈለገው መጠን ቸኮሌት አልተመገቡም።

በጥናቱ ከተሳተፉት መካከል በሳምንት ውስጥ 28 ነጥብ 35 ግራም ቸኮሌት የተመገቡት በወር አንድ ጊዜ ወይም በጭራሽ ከማይመገቡት ይልቅ የበሽታው ተጋላጭነታቸው ቀንሶ ታይቷል ነው የተባለው።

በዚህም በ17 በመቶ በጭንቅላት ውስጥ ለደም መፍሰስ በሽታ የመጋለጥ እድላቸው መቀነሱ በጥናት ውጤቱ ላይ ተገልጿል።

በሽታው በአብዛኛው በእድሜ ገፋ ያሉት ላይ እንደመከሰቱ መጠንም በዚህ ጥናት የተገኘው ውጤት መልካም የሚባል መሆኑን የጥናት ቡድኑ መሪ ዶክተር ኤልሳቤት ሞስቶፍስኪ ተናግረዋል።

                                     

የጥናታችን ውጤትም ቸኮሌትን መመገብ ለጤና ያለውን ጠቀሜታ ያሳየ ነው ብለዋላ ተመራማሪዋ።

በቸኮሌት ውስጥ የሚገኙት ንጥረ ነገሮች የደም ቧንቧዎች በአግባቡ እንዲሰሩ ያግዛሉ፤ ከዚህ አንጻርም አደገኛውን በጭንቅላት ውስጥ ደም የመፍሰስን አጋጣሚ ይቀንሳሉም ነው የተባለው።

እንደ ባለሙያዎች ገለጻ ቸኮሌት ሲመገቡ የተሻለና የተስተካከለ የደም ዝውውር ይኖራል፤ የደም ቧምቧ መጥበብና መዘጋት አጋጣሚም ይቀረፋል።

ያልተለመደና እንግዳ የሆነ የልብ ምት፣ የደም መርጋትና ብሎም በጭንቅላት ውስጥ ደም የመፍሰስ አጋጣሚ እድሜ እየገፋ ሲሄድ የሚከሰት የጤና ችግር ነው።

አሁን ተመራማሪዎች አገኘነው ያሉት ውጤትም መነሻ በመሆኑ ሰፋ ያለ ተጨማሪ ምርምር ይደረጋል ተብሏል።

ግን ቸኮሌትን ቢያንስ በሳምንት ሶስት ቀን አንድ አንድ መመገቡ መልካም መሆኑንን አስምረውበታል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement