የዛሬ የዕለተ ሐሙስ ሐምሌ 20 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች::

                                           

የኮሪያ አለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ለሚገኙ የልብ ታማሚ ህፃናት ህክምና ሊያደርጉ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

በአቃቂ የሚገኘው ትንሹ ድልድይ ከአገልግሎት ውጭ ሆነ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

በቅርቡ ከአደጋ መዝገብ በተፋቀው በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የብርቅዬ የዱር እንስሣት ብዛቱ እየጨመረ መሆኑ ተነገረ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ከተሰማሩ ተቋራጮች 7ቱ ውላቸው መቋረጡ ተሠማ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

በስርቆት ወንጀል የተጠረጠረው ተከሣሽ የፖሊስ አባል በእሥር ተቀጣ፡፡ (ምህረት ስዩም)

ለኢትዮጵያ ባለውለታ የውጭ አገር ሰዎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት ሊሰጣቸው ነው፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)

በዚህ አመት ከቆዳና የቆዳ ግብዓቶች የወጭ ንግድ ለማግኘት ከታቀደው ገቢ የተሳካው 42 በመቶው ብቻ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

ዘንድሮ በእሣትና ድንገተኛ አደጋዎች 82 ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የስጋ፣ የማርና ሰም የእንስሣት መኖና የወተት ምርቶችን ወደ ውጭ ልካ 104 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች ተባለ፡፡ (አስፋው ስለሺ)

የስዊድን መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚሰሩ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችና በድህነት ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን መደገፊያ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡ (ምህረት ስዩም)

መንግሥት በ2009 በጀት ዓመት የፈፀመው ግዢ ከቀዳሚው ዓመት በግማሽ ያነሰ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር የታለመ መርሐ-ግብር ይፋ ተደረገ፡፡ (ምሥክር አወል)

 

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

 

Advertisement