የዛሬ የዕለተ ረቡዕ ሐምሌ 19 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች::

                                           

18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ጊዜያዊ የሰልጣኞች ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ነፃ የጉበት ምርመራ ላደርግ ነው አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ቁጥር መጨመር ተጨማሪ መጠለያ ሊያስገነባ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

በኢትዮጵያ ካለው የመሬት ሽፋን ለጥጥ ምርት የዋለው አነስተኛ ነው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)

አሮጌው የአቃቂ ድልድይ በመሰነጣጠቅ ላይ በመሆኑ ከሦስት ቶን በላይ ክብደት ያላቸው ተሽከርካሪዎች እንዳይተላለፉበት ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ተለዋጭ መንገዶችን ሰጥቷል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

የቅድስት-ማርያም ዩኒቨርስቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ ጥናቶች ለሚወጡ ፖሊሲዎች ግብዓት እንዲሆኑና በሥራ ላይ ያሉም ውጤታማ ስለመሆናቸው የሚረጋገጥበት አሰራር እንዲለመድ እየሰራሁ ነው አለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)

አዋሽ ባንክ ለመረጣቸው ሰባት ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ልገሳ አደገ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 34 ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ባለሃብቶችና ደላሎች በትላንትናው እለት በቁጥጥር ስር መዋል ጀምረዋል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእንስሣት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የእንስሣት መድኃኒት ፋብሪካዬን ግንባታ እያጠናቀቅኩ ነው አለ፡፡ በ54 ሚሊዮን ብር የተገዛው መሣሪያም ከጂቡቲ ወደብ ደርሷል ብሏል፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)

በአዲስ አበባ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ከ130 ሺ ተመዛኞች 80 ሺ 577ቱን ወደ ኢንዱስትሪው መላኩን ተናገረ፡፡ (ምሥክር አወል)

በሰንጋተራና ክራውን ሳይቶች በተገነቡት የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ 320 ንግድ ቤቶች በቅርቡ ጨረታ ይወጣላቸዋል ተባለ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የመንን ጎበኙ፡፡ (አስፋው ስለሺ)

ባለቤቱን የገደለው ግለሰብ በእድሜ ልክ እሥራት ተቀጣ፡፡ (ምህረት ስዩም)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement