SPORT: ጁቬንቱስ የበርናንዲችን ዝውውር ማጠናቀቁ ተረጋገጠ::

                                 

ጁቬንቱስ በአምስት አመታት የውል ስምምነት ፌደሪኮ በርናንዲችን ከፊዮረንቲና በ 35.7 ሚሊዮን ፓውንድ ማስፈረሙን ማረጋገጫ ሰጥቷል።

በፖላንድ በተደረገው ከ 21 አመት በታች የአለም ሻምፒዮና ሀገሩ ጣሊያንን ወክሎ መጫወት የቻለው በርናንዲች የቱሪኑ ክለብ ፒኤስጂን በወዳጅነት ጨዋታ ከማስተናገዱ በፊት በዛሬው ዕለት ማክሰኞ ወደ አሜሪካ ቦስተን ከተማ በማምራት አዲሱ ቡድኑን ይቀላቀላል። 

ጁቬንቱስ የተስፈኛውን ታዳጊ ዝውውር አስመልክቶ በድረገፁ በለቀቀው መግለጫ በተከታዮቹ ሶስት አመታት ለተጫዋቹ ዝውውር 40 ሚሊዮን ዩሮ ለመክፈል መስማማቱንና በቀጣይ ተጫዋቹ በቱሪኑ ክለብ የሚሸጥ ከሆነም ለፊዮረንቲና የሚከፈለው ክፍያ በ 10 በመቶ እንዲያድግ ከስምምነት ላይ መደረሱን አያይዞ ገልጿል። 

በቱስካኒ የተወለደው በርናንዲሽ በዘጠኝ አመቱ የፊዮረንቲና ታዳጊ ቡድንን የተቀላቀለ ሲሆን በተፈጥሮ ባለው የማጥቃት ክህሎትም በላ ቪዮላ አካዳሚ በስኬት አልፎ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል። 

ጁቬንቱስ በርናንዲሽን ለማስፈረም የቻለው የቼኩን ተጫዋች ፓትሪክ ሺቺክን ለማዘዋወር የነበረውን ስምምነት ካፈረሰ በኋላ መሆኑ ይታወቃል።  

ምንጭ:- ኢትዮአዲስ ስፖርት

Advertisement