የዛሬ የዕለተ ሐሙስ 13 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎች

       

የዛሬ የዕለተ ሐሙስ 13 ቀን 2009 የሸገር ወሬዎቻችን፣
በህገ-ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጣ የነበረ 240 ኩንታል ቡናን ጨምሮ የተለያዩ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ እቃዎች መያዛቸውን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
በዘውዲቱ ሆስፒታል ለሚካሄደው የኩላሊት እጥበት ህክምና /ዲያሊስስ/ ተጨማሪ 14 ማሽኖች ተገዝተው ሊጨመሩ ነው ተባለ፡፡ (ትዕግስት ዘሪሁን)
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተማዋን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ዘመናዊ የቁጥጥር መሣሪያዎችን ማደራጀት መላ ካላቸው ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ (አስፋው ስለሺ)
በጥብቅና የሚተዳደሩ ሞያተኞች አመታዊ ግብር ለመክፈል ተቸገርን ሲሉ ቅሬታቸውን ለሸገር አቀረቡ፡፡ ቅሬታ የቀረበበት አካል በበኩል ትዕዛዝ እየጠበኩ ነው ብሏል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
በኢትዮጵያ መዋለ ነዋይ ፈሰስ በማድረግ የቻይና ኩባንያዎች ቀዳሚ ናቸው ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
በዚህ ዓመት ከ59 ሺ በላይ ቱሪስቶች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ፓርኮችና የዱር እንስሣት መጠለያዎች ጎብኝተዋል ተባለ፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
አዲስ አበባን መልሶ ለማልማት ከ3 ሺ 500 በላይ ቤቶች ፈርሰዋል ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን በሂሣብ ምርመራ የተገኘበትን ጉድለት ለማስተካከል ኮሚቴ አቋቁሞ እያጣራ መሆኑን ተናገረ፡፡ (ዮሐንስ የኋላወርቅ)
ኢትዮጵያ ከጎረቤትና ከሌሎች ሀገራት ጋር የሚኖራትን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች መሠረት ያደረገ ሥልጠና ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተዘጋጀ፡፡ (የኔነህ ሲሣይ)
አዲስ አበባ ውስጥ በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ 4 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ተመረቁ፡፡ (ንጋቱ ረጋሣ)

ምንጭ:- የሸገር FM 102.1 ሬዲዮ

Advertisement