ዛሬ የኔልሰን ማንዴላ የልደት በዓል በደቡብ አፍሪካ እየተከበረ ነው::

                                      

የዛሬው የኔልሰን ማንዴላ (የማዲባ) የልደት በዓል በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተከበረ ነው!!
ደቡብ አፍሪካውያን የሃገራችን አባት ብለው የሚጠሩዋቸውን የማዲባን የልደት በዓል በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ሲያከብሩ ውለዋል።
ማዲባ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ዛሬ ዘጠና ዘጠነኛ ዓመታቸውን ያከብሩ ነበር። እኤአ በ2013 ዓ.ም በዘጠና አምስት ዓመታቸው ነው፣ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት።
በ2009 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሃምሌ አሥራ ስምንት የኔልሰን ማንዴላ ዓለም አቀፍ ቀን (Nelson Mandela International Day) ተብሎ በዓለም ዙሪያ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲከበር አውጇል። 

ምንጭ:- ቪ ኦ ኤ(VOA)

Advertisement